Wednesday, December 28, 2011

ምን ዓይነት ጸሎት በየትኛው ሰዓት ልጸልይ? ኢትዮጵያውያንና የያዕቆብ የመጨረሻ ልጅ የቢኒዖን (ብንያም)ነገድ

የጸሎት ቦታ እንዴት ላዘጋጅ?

1. የጸሎት ጊዜያት

ልበ አምላክ ነቢየ ልዑል ቅዱስ ዳዊት”ስብዓ ለእለትየ እሴብሐከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ ፣ስለ ጽድቅህ ፍርድ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለው”/መዝ 118-164/ብሎ እንደተናገረ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ሰባት ጊዜ በየእለቱ እንዲጸልይ ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡ሰባቱ የጸሎት ጊዜያትም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1.1 ጸሎተ ነግህ

ቅዱስ ዳዊት “አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ” መዝ 62÷11 እንዳለ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ፣ከመኝታችን ስንነሳ ምንጸልየው የጸሎት ዓይነት ጸሎተ ነግህ ይባላል፡፡በዚህ ጊዜ የሚከተሉትን ምስጢራት እያሰብን መጸለይ ይገባናል፡፡
.ሌሊቱን አሳልፎ ቀኑን ስለተካልን እያመሰገንን ወጥተን እስክንገባ በሰላም ጠብቆ ውሎአችንን የተባረከ እንዲያደርግልን እንጸልያለን።

·የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረበትም ሰዓት በመሆኑ ያንን እያሰብን እንጸልያለን፡፡
·የሰውን ልጅ በመዓልትና በሌሊት የሚጠብቁ መላእክት ለተልዕኮ ሲፋጠኑ የሚገናኙበት ሰዓት ነው፡፡የሌሊቱ መልአክ ሲሄድ የቀኑ መልአክ ሲቀርብና ሲተካ የሚገናኙበት በመሆኑ በዚህም ሰዓት እንጸልያለን፡፡

.ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች በደል በጲላጦስ አደባባይ የቆመበት ሰዓት በመሆኑ እንጸልያለን።

1.2 ጸሎተ ሠለስት (3 ሰዓት)

ከነግህ በመቀጠል የምንጸልየው ጸሎት ጸሎተ ሠለስት (የሦስት ሰዓት) ጸሎት ይባላል፡፡ይህ የጸሎት ጊዜ
. ሔዋን የተፈጠረችበት
. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት የሰማችበት
. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት
. ነቢዩ ዳንኤል ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ መልሶ የቤቱን መስኮት ከፍቶ የጸለየበት
. ለአባቶቻችን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት /በኢየሩሳሌም ጸንተው በመቆየታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይህንን ታላቅ ጸጋ የተቀበሉበት /ሰዓት ነው፡፡

1.3 ቀትር(6 ሰዓት)

በእለቱ እኩሌታ ላይ የምናገኘው ይህ ሰዓትም እንደዚሁ የጸሎት ጊዜ ነው፡፡ይህም ጊዜ
.ሰይጣን አዳምን ያሳተበት
.በዕፀ በለስ ምክንያት ለስሕተት የተዳረገውን አዳምን ለማዳን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ የዋለበት
.የቀን እኩሌታ በመሆኑ የፀሐይ ሙቀት የሚያይልበት የሰው ልጅ ለድካም የሚዳረግበት በዚህም ምክንያት አጋንንት የሚበረታቱበት ጊዜ ነው።
.ስለዚህ የአዳምን ስሕተት፣ የዳግማዊ አዳም የኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀልና መሞት፣እያሰብን የቀን እኩሌታ በመሆኑ መዳከማችንን ተገን አድርጎ አጋንንት እንዳይሰለጥንብን እየለመንን እንጸልያለን፡፡

1.4 ተሰዓተ ሰዓት (9 ሰዓት)

ዘጠኝ ሰዓት ላይ አራተኛውን ጸሎት እናደርሳለን።በዚህ ጊዜ
.ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ነጻ ለማውጣት በፈቃዱ ቅዱስ ሥጋውን ከቅድስት ነፍሱ የለየበት ሰዓት ነው።
·ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን በጎም ሆነ ክፉ ተግባር ወደ ፈጣሪ የሚያሳርጉበት ነው
·ቆርኖሌዎስ የተባለ መቶ አለቃ በጸሎት ጸንቶ ደጅ ሲጠና ከሰነበተ በኋላ ከፈጣሪው ምላሽ ያገኘበት ሰዓት ነው (ሐዋ 10÷ 9)
በዚህ ጊዜ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ እና ሞት አያሰብን ቅዱሳት መላእክት ከፈጣሪያቸው እንዲያስታርቁን እየለመንን የቆርኖሌዎስ እድል እንዲገጥመን እየተማጸንን እንጸልያለን፡፡

1.5 ጸሎተ ሰርክ (11 ሰዓት)

አምስተኛው የጸሎት ጊዜ የሠርክ ጸሎት ነው፡፡ስለዚህ የጸሎት ሰዓት ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል፡፡”ጸሎቴን እንደ ዕጣን በፊትህ ተቀበልልኝ እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን” (መዝ 140 ÷2)
·ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ወደ መቃብር የወረደበት ሰዓት ነው፡፡ (ማቴ. 27÷ 57)

1.6 ጸሎተ ንዋም (የመኝታ ጊዜ ጸሎት)

ይህ ጊዜ ዕለቱን በሰላም አሳልፈን ለሌሊቱ ዕረፍት የምንዘጋጅበት ነው፡፡በሰላም ላዋለን ፈጣሪ በሰላም አሳድረን ብለን ራሳችንን በእምነት የምናስረክብበት ነው፡፡እኛ ተኝተን የሚሆነውን አናውቅም እርሱ ግን የማያንቀላፋ እረኛ ስለሆነ ይጠብቀናል።ስለዚህ ከመተኛታችን በፊት ሊሌሊቱን እንዲባርክልን እንጸልያለን።
በዚህ ጊዜ፡-
·ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ ዛሙርቱን በጌቴሴማኒ ጸሎት አስተምሯቸዋል፡፡
·ቀኑ አልፎ በሌሊቱ ይተካል
ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለጸሎት ማስተማሩን እያሰብን እንጸልያለን፡፡ሰላም አሳድረንም ብለን ለፈጣሪ ራሳችንን በእምነት አደራ እናስረክባለን፡፡

1.7 መንፈቀ ሌሊት (እኩለ ሌሊት)

·እኩለ ሌሊትም እንደ ቀናቱ የጸሎት ሰዓታት የተለያዩ ትርጉሞች አሉት ።
ቅዱሰ ዳዊት ‘’መንፈቀ ሌሊት እትነሣእ ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ”“ስለ ጽድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት አመሰግነህ ዘንድ እነሳለሁ”/መዝ 118-62/በማለት ይህ ሰዓት ከእግዚአብሔር ጋራ የሚነጋገርበት እንደሆነ ገልጿል፡፡

· ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ዋሻ የተወለደበት ሰዓት ነው።
· ሞትን ድል አድርጎ በታላቅ ኃይልም የተነሳው በሌሊት ነው።
· ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ለፍርድ ሚመጣበትም ሰዓት ነው።
ከዚህ የተነሳ ለእኛ ሲል ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን በማሰብ ሞትን ድል እንደነሳልንም አስበን በማመስገን ዳግመኛ ለፍርድ ሲመጣ በቀኙ ከሚያቆማቸው ወገን እንዲያደርገን እየለመንን በዚህ ሰዓት እንጸልያለን፡፡

ሰባቱን የጸሎት ጊዜያት ጠብቀን መጸለይ ካልተቻለንስ?

በሰባቱ የጸሎ ሰዓታት የታቻለንን ያህል እንድንጸልይ ታዘናል፡፡እነዚህን የጸሎት ሰዓታት በገዳም ያሉ መነኮሳት በየበረሃው የሚዞሩ ባሕታውያን ይጠብቋቸዋል፡፡ይጸልዩባቸዋልም፡፡በከተማ በሥራ ምክንያት ሩጫ በዝቶበት በሁሉም ሰዓት መጸለይ የማይችል ክርስቲያን ግን ቢያንስ በማለዳ ከእንቅልፉ ሲነሳ እና ማታ ወደ መኝታው ሲያመራ መጸለይ ይገባዋል።ጠዋት እና ማታ በመጸለይ ከፈጣሪ ጋራ ያለው የአባትና ልጅ ግንኙነት እንዳይቋረጥ ማድረግ ይገባዋል፡፡
ምን እንጸልይ?
በመደበኛነት ልንጸልያቸው የሚገቡ ጸሎታት /በቤተክርስቲያናችን አባቶች በገዳማቱ በአድባራቱ የሚዘወተሩ እለታዊ ጸሎታት/ እነኚህ ናቸው፡፡

1.መዝሙረ ዳዊት

መዝሙረ ዳዊት በገዳማት ከሚኖሩ አበው መነኮሳት ባህታውያን ጀምሮ በካህናት፣ምእመናን በሁሉም ዘንድ በየእለቱ የሚጸለይ ጸሎት ነው።አባቶች ከፊደል ቆጠራው ቀጥሎ ዳዊቱን ያጠኑና ከዚህ ጊዜ ጀምረው እየደገሙት፣እየጸለዩበት ይኖራሉ።ዳዊት ሳይደግሙ ወደ ዕለታዊ ተግባራቸው አይሰማሩም።መዝሙረ ዳዊት እንደሌሎች ጸሎታት ሁሉ በየዕለቱ ተለይቶ የሚጸለይ አለው።ቀጥለን እንመልከት
ሰኞ ከ 1 - 30፣ማክሰኞ ከ 31 – 60፣ረቡዕ ከ 61 – 80፣ሐሙስ ከ 81 – 110፣አርብ ከ 111 – 130፣ቅዳሜ ከ 131 – 150
እሁድ- ጸሎተ ነቢያት እና መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ይጸለያል፡፡

አንድ ንጉሥ
መዝሙረ ዳዊትን ስንጸልይ ለዕለቱ የታዘዘውን ሃያ እና ሰላሳ መዝሙር ማድረስ ባንችል እንኳን አንድ ንጉሥ ማድረስ ይገባናል። አንድ ንጉሥ የሚባለው፡-አስር መዝሙር ነው፡፡ለምሳሌ ሰከኞ አንድ ንጉስ ለማድረስ ከፈቀዱ ከ 1 – 10 ያለውን ያደርሳሉ፡፡ከማክሰኞ ከሆነ ደግሞ ከ 30 -40 ያውን የመጀመሪያውን አስር መዝሙር ያደርሳሉ ማለት ነው፡፡ይህን ሁሉ ማድረስ ያልተቻለው ግን የተወሰኑ መዝሙራትን መርጦ በየእለቱ ያደርሳል፡፡

2. ውዳሴ ማርያም
ውዳሴ ማርያም ከተቻለ የሰባቱን ዕለታት ካልተቻለ የእለቱን ማድረስ ተገቢ ነው።የዘወትር ጸሎት ካደረስን በኋላ የዕለቱን ውዳሴ ማርያም አድርሰን ይዌድስዋ መላዕክትን ደግመን ከእመቤታችን በረከት ተሳታፊ መሆን ተገቢ ነው፡፡በዋልድባ የሚኖሩ መነኮሳት ውዳሴ ማርያም ከቅዳሴ ማርያም ሳያደርሱ ውለው አያድሩም፡፡በየአብነት ትምህርት ቤቱ የሚገኙ መምህራንና ተማሪዎች እና በየገዳማት ያሉ መነኮሳት ሁሉ ውዳሴ ማርያምን በየዕለቱ ያደርሳሉ፡፡እኛም ከአበው ተምረን ማታ ከመኝታ በፊት ወይም ጠዋት ስንነሳ ይህን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው፡፡

3. ወንጌል ዘዮሐንስ
የዮሐንስ ወንጌልን በየምዕራፍ ከፋፍለን በየእለቱ ማንበብ ሌላው ጸሎት ነው፡፡አባቶች ይህንን ጸሎት በየእለቱ እያደረሱ ብዙ ተጠቅመውበታል።

4.ሌሎች ጸሎታት
ውዳሴ አምላክ፣ ሰኔ ጎለጎታ፣ መልክአ ኢየሱስ፣ መልክአ ማርያም ፣ በመዝገበ ጸሎት እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍት ላይ ያሉትን ሌሎች ጸሎታት፣እንዲሁም ገድላት፣ተአምራትን፣እንደ ችሎታችን በየዕለቱ እናደርሳለን፡፡ቢያንስ ግን ይህ ሁሉ ባይሆንልን ከላይ የጠቀስነውን የመዝሙረ ዳዊትና ፣ውዳሴ ማርያምን ጸሎት ማድረስ ይገባናል፡፡

አጭር ጸሎት
በተቻኮልን እና መጻሕፍትን ለማንበብ ጨርሶውን ጊዜ በማይኖረን ሰዓት ይህንን እንድንጸልይ አንዳንድ አባቶች ይመክሩናል።አቡነ ዘበሰማያት፣ጸሎተ ሃይማኖት፣ሰላም ለኪ /ስለ ውዳሴ ማርያም ፈንታ/፣አቡነ ዘመሰማያት፣አንድ ከመዝሙረ ዳዊት/ መዝሙር 150/ በመዝሙረ ዳዊት ፈንታ/በመጨረሻም አቡነ ዘበሰማያት ማድረስ ብንችል መልካም ነው ።ጸሎተ ሃይማኖት የህይማንት መግለጫ በምህኑ እንጸልየዋለን። በመካከል ሰላም ለኪ በመድገማችንም የውዳሴ ማርያም በረከት ይደርሰናል። መዝሙረ ዳዊት 150 ስናደርስ ደግሞ ሁሉንም መዝሙራት የደገምን ያህል ይሆንልንና የዳዊቱን በረከት እናገኛለን፡፡ይህንን ሁሉ ማድረስ ካልተቻለን ግን ቢያንስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን አቡነ ዘበሰማያት ብለን ከቤታችን ልንወጣ ይገባናል።አጭር ጸሎት ከሥፍራ ሥፍራ ሊለያይ ይችላል፡;ዘጠኝ ሰላም ለኪ፣አስራ ሁለት አቡነ ዘበሰማያት በገዳማት ያሉ አበው ያደርሳሉ።

የጸሎት ቅደም ተከተል
አቡነ ዘመሰማያት: አንድ ከመዝሙረ ዳዊት:ውዳሴ ማርያም: እና ሌሎችም:ቀጥሎም አቡነ ዘመሰማያት በ እንተ እግዘዕትነ ማርያም: ጸሎተ ሃይማኖት በመጨረሻም አቡነ ዘመሰማያት ኪርያላይሶን 41 ግዚ::


አጭር ጸሎትን እነደ መደበኛ ማድረግ ለፈተና ያጋልጣል

አጭር ጸሎት የምንጸልየው በጣም በተቸገርንበት፣ጊዜ ባጣንበት ሰዓት ነው።ይህንን ጸሎት እንደመደበኛ ይዞ በየእለቱ አንድ አቡነ ዘበሰማያት ብቻ መድገም ግን ስንፍና እንዳይሆን ያስፈራል።ይልቁንም በክርስትና ሕይወት ጅማሬ ላይ ያሉ ምእመናን/ወጣንያን/ክርስትናውን እስኪላመዱ ጸሎታቸው አጭር ሊሆን ይችላል።እየቆዩ ሲሄዱ ግን በጸሎት እየበረቱ ወደ መደበኛው ጸሎት መድረስ አለባቸው።ሁል ግዜ ወተት መመኘት ሁል ግዜ አልበረታውም እያሉ አጭር ጸሎት እያደረሱ መተኛት ተገቢ አይደለም።ይህ አይነቱ አካሄድ የእግዚአብሔርን ቸርነት ለስንፍና ምክንያት አድርጎ መጠቀምም ነው።ከዚህ ጋር በቤተክርስቲያን አገልገሎት ላይ ያለንም ዳዊት መድገም ውዳሴ ማርያም ማድረስ ይጠበቅብናል።የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ፣ዲያቆናት፣ቀሳውስት፣ሰባክያነ ወንጌል፣መዘምራን……እነዚህን ጸሎታት መጸለይ ይጠበቅባቸዋል።አልያ ግን እያወቅን ጸሎት ማድረስ እንዳለብን ብዙ ጊዜ ተምረን እንዳልተምርን ቸል ብንል ለፈተና መጋለጥ ይመጣል።ከእግዚአብሔርም ቸርነት እንድንርቅ ያደርገናል።

አቡነ ዘበሰማያት የጸሎታችን መነሻና መድረሻ ጸሎት ስናደርስ የጸሎታችን መነሻ (መጀመሪያ) አቡነ ዘበሰማያት ነው፡፡በመካከል ጸሎት አቋርጠን ከሰው የምንነጋገርበት ጉዳይ ቢገጥመን በአቡነ ዘበሰማያት ማሰር ተገቢ ነው፡፡በአቡነ ዘበሰማያት አስረን የገጠመንን ጉዳይ ፈፅመን እንመለሳለን፡፡ከዚያም አቡነ ዘበሰማያት ብለን ካቆምንበት እንቀጥላለን።ጸሎታችንን በአቡነ ዘበሰማያት ሳናስር በመሃል እንዳሻን እንዳናቋርጥ አበው ያስተምሩናል፡፡

የማህበር ጸሎት

በቤታችን ከምንጸልየው ጸሎት በተጨማሪ በቤተክርስቲያን ተገኝተን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው።ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት እንደመሆና በእርሱአ የሚጸለይ ጸሎት ከጸሎታት ሁሉ የላቀ ነው።በካህናት እየተመራ ፣በሕብረት ሆነን የምናደርሰው በመሆኑ ታላቅ ኃይል አለው።እግዚአብሔር በቤተ መቅደስ የምንጸልየውን ጸሎት እንደሚሰማ ሲያመለክተን እንዲህ በማለት ነግሮናል።”አሁንም በዚህ ሥፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ ፣ጆሮቼም ያደምጣሉ።ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም ዓይኖቼ እና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።”/2 ዜና መዋ 7-15/ ከዚህ አንጻር በቤተ መቅደስ እየተገኘን መጸለይ ተገቢ ነው።በሰንበት ቀን ኪዳን ማድረስ ፣ ቅዳሴ ማስቀደስ የመጀመሪያው እና ዋነኛው ተግባራችን መሆን አለበት።በሰንበት ያለ በቂ ምክንያት ቅዳሴ የሚያስታጉል በቀደሙ አባቶች /አባ ሚካኤል ወአባ ገብረኤል/ቃል መወገዙን የተአምረ ማርያም መቅድም ይነግረናል።ከዚህ ጋር በሰዓታት ፣በማኅሌት ጸሎታት ላይ በመገኘት ቤተ ክርስቲያናችን ካዘጋጀችልን የማይጠገብ ማእድ ልንሳተፍም ይገባናል።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች የሃይማኖታችን ፍጹም ፍቅር የሚኖረን ከእነዚህ ጸሎታት ጋር ስንተዋወቅ ነው።አልያ የእንጀራ ልጅ መሆን ይመጣል።የመናፍቃንን አዳራሽ መናፈቅ ይመጣል።

ከላይ በተመለከተው የጸሎት ጊዜ እየተጠቀምን፣የጸሎት ዓይነቶችንም በምንችለው መልኩ እያደረስን፣በቤተ መቅደስ እየተገኘን ኪዳን እያደረስን፣ቅዳሴ እያስቀደስን ከፈጣሪን ጋራ እለት እለት እንነጋገር ጸሎት ከሌለ መንፈሳዊነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ከጄነሬተሩ ተቋርጦ ገመዱ ተበጥሶ ብቻውን እንደተንጠለጠለ አምፖል መሆን ይመጣል፡፡ስለዚህ በርቱ  ጸልዩ ፈጣሪ ለሁላችንም ብርታቱን ያድለን፡፡አሜን

የጸሎት ቦታ እንዴት ላዘጋጅ?

ስለ ጸሎት እና ክርስቲያናዊ ህይወት 
http://www.eotc-mkidusan.org/site/images/stories/pdfs/Kirstianawi_Hiwot_Ena_Migbar3.pdf

ኢትዮጵያውያንና የያዕቆብ የመጨረሻ ልጅ የቢኒዖን (ብንያም)ነገድ 
 ሁሉንም ከመምህር ግርማ ጥልቅ መንፈሳዊ ትምህርቶች

ቢኒዖኒ ማለት የጭንቅ/ሙት ልጅ ማለት ሲሆን እናቱ እሱን ስትወልድ በመጨረሻ ጣሯ ያወጣችለት ሥም ነው፡፡ ቢኒዖኒ እንደ ወንድሙ ዩሴፍ እናቱ በበረከትና በእግዚአበሔር አምልኮት ሳይሆን የፀነሰችው የአባቷን የላባን ጣዖት ሰርቃ በነበረበት ወቅትና ያዕቆብ ቤተሰቡን ይዞ ከላባ በተለየ ጊዜ ላባ ጣዖቴን ሰረቀሃል ብሎ ሲከተለው ያዕቆብም ከቤተሰቤ ያንተን ጣዖት የሰረቀ/የምታገኝበተ ሰው እሱ ይሙት (ዘፍጥረት 31፡ 32)ብሎ ከረገመ በኋላ ነው (ሙሉ ታሪኩ ዘፍ 31፡ 22-42)፡፡ እንደ ያዕቆበም እርግማን ራሔል ቢኒዖኒን (ብንያምን) ስተወልድ በጭንቅ ሞተች!! ምንም እናቱ ቢኒዖኒ (የጭንቀቴ ልጅ) ብትለውም አባቱ ይወደው ነበርና ብንያም (የቀኝ ክንዴ) ብሎት ነበር (ዘፍ 35፡ 16-21)፡፡ ሆኖም ግን በኋላ ያዕቆብ የልጆቹን መጻኢ ዕድል ለመወቅ እግዚአብሔርን ሲጠይቅ የብንያም ዕጣፈንታ በጣም የሚያሳዝን እንደሆነ እግዚአብሔር ነግሮት ብንያም ነጣቂ ተኩላ ነው (ዘፍ 49፡ 27) ብሎ ነበር፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ የብንያም ነገድ አሳዛኝ ታሪክ ያለው ነው፡፡ምክነያቱም በዘር የተላለፈ የክፉ መንፈስ (እናቱ ራሔል ያመለከችወ ጣዖት) እንደሆነ የሀይማኖት ጠባብቶች/ፈላስፋዎች ይናገራሉ፡፡ ይህ የክፉ መንፈስ ዘር ከዘመናት በኋላ የብንያም ነገድ የሆነውን ንጉሱ ሳዖልን እንዴት እንደጣለው መጽሐፍ (ሳሙ ቀ ዳማዊ 31፡ 1-13) እንድናሰተውል ይጋብዘናል (ሙሉ ታሪኩ መ.ሳ ቀዳማዊ)፡፡ ኋላም በክርስቶስ ዘመን የብንያም ነገድ የሆነውን ሳዖል (ኋላ ቅዱስ ጳውሎስ) የቱንም ያህል ለእግዚአብሔር ቀናኢ ቢሆንም ክርስቶስን ለማሳደድ ዳርጎት እንደነበር፣ ልዑል አምላክ ግን ለእሱ ያለውን ቀናኢነት ስለተመለከተለት ለጥፋት ሲጓዝ መንገድ እንደዘጋብት፣ አይኑን እነዳሳወረው ይድንምና ማድረግ የሚገባውን ያውቅ ዘንድ ወደ ካህኑ ሐናንያ እንደላከው፣ ከአይኖቹም ቅርፊት እንደተነሳ መጽሐፍ ይናገራል(ሐዋ 9፡ 1-21)፡፡ ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላና ቅዱስ ጳውሎስ በጨርቁ ሳይቀር የሌሎችን ደዌና ርኩስ መንፈስ እያሰወገደ አንኳን ይህ ክፉ መንፈስ እጅግ ሲፈታተነው እንደነበር መጽሐፍ ይናገራል፡፡ በመጨረሻ ግን ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን የክፉ መንፈስ ዘር ለማቋረጥ የቻለ የብንያም ወገን ሆኗል፡፡

በዘር የሚተላለፉ ሚስጥራዊ የጤና ችግሮችና የክፉ መናፍስት ጥቃቶች (Genetically transferable enigmatic health challenges vs evil spirit attacks) ሁላችንም በአፅእኖት ልናስተውለው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ብዙ ችግሮቻችን ከዘር የተወረሱ ተብለው በስያሜና በይሁንታ ተሸፋፍነው የክፉ መናፍሰት ሴራዎች ለመሆናቸው ጉዳይ ሳንሰጣቸው ቀርተናል፡፡
• አይናችን ቢፈዝ የዘር ተብለን መነፅር መሰካት፡፡ መነፅሩ ባልኖረበት ዘመን በኖሩ ዘሮቻችን (ወገኖቻችን) የማይታወቀው የእይታ ችግር (Sight) ዛሬ ብዙዎቻችንን እንዳጠቃን እናስተውል፡፡ መነፅሩ ባይኖር ምን ልንባል ነው? አይነስውር?
• ነርቭ፣ስኳር፣ደምግፊት፣ ኦቲዝም/ዳይሜንሺያ፣ አስም፣አለርጂ፣ ለምፅን ጨምሮ ልዩ ልዩ የቆዳ ችግሮች ወዘተ ሁሉ ከዘር ጋር እንሚገናኙ ሳይንስ ይናገራል፡፡ ነገሩ ልክ ነው ግን ሳያንስ ችግሩ በዘር በሚመጣ የመንፈስ ጥቃት ሳይሆን በዘር በሚተላለፍ ደካማ ዘረ-መል (gene) እንደሆነና ለማቋረጥ ምናአልባት ዘረ-መሎቹን ማሰወገድ (gene knock out) አመራጭ ነው ይለናል፡፡ የስነሕይወቱ ሳይንስ (Biology) ይህን ይበል እንጂ በተግባር ግን ጉዳዩ ውስበስብና የማይቻልም ነው፡፡

• አንዴ የዘር (genetic) ተብሎ ተፈቅዶለታልና ይህ ክፉ መንፈስ ከኛ በሚመጡት የልጅ ልጆቻችን እንዲቀጥል ፍቃድ መስጠታችንን አንዘንጋ፡፡ እንደ ጳውሎስ እሰካለቋረጥነው ድረስ እንሚቀጥል ልብ ልንል ይገባል፡፡!
እኔም በአቅሜ በማስተዋል እንድንሔድ እናገራለሁ፡፡ ሊያውም ሳልወድ በግዴ! ለካ እንዲህም አለ! ለልዑል አመላክ ምሰጋና ይግባውና እኛን ሆኖ ተግልጦ በምደር የተናገረውንና የሠራውን ብዙዎቻችን ሳንወድ በግዳችን ዛሬ አይተን እንድናምን አድርጓል፡፡ ምንም ሳያዩ ያመኑ ብፁዐን ናቸው ቢባልም፡፡ አይተን ላመንውም እግዚአበሔር ይመስገን! አይተውም አናምንም ብለው የተሰጣቸውን እድል አምቢ ያሉ ብዙዎች ይልቁንም የሚበልጡት ናቸውና፡፡ ማንም ሰው (ከለየላቸው በጣም ጥቂቶች በስተቀር) በእግዚአበሔር ታምናለህ ቢባል መልሱ አዎ ለመሆኑ አያከራክርም፡፡ እውን ግን አምናለሁ የሚለው ሁሉ ያምናል?! ከጥቂቶች በቀር አጠያያቂ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እግዚአበሔርን አምናለሁ ብሎ የሚለው በዙ ሰው ሰይጣን አለ የለም ሲሉት የለም ብሎ የሚያምን መሆኑ በራሱ የእግዚአበሔርንም ስለሚፈራ ነው እንጂ በትክክለ አንዳለ ስለሚያምን አይደለም አግዚአበሔር አለ የሚለው፡፡ የእግዚአብሔርን ሀልዎት የሚያምን ሰይጣን እንዳለ አሳምሮ ያውቀዋልና! በሌላ መልኩ ስንታይ ደግሞ ከእግዚአበሔር ኃይል ይልቅ የሰይጣንን እገዛ አበዝተን የምነፈልግ ለመሆኑ በደንብ የምናስተውል ከሆነ ጠንቋይ፣ ቃልቻ፣ ደብተራ ወይም ሌላ አለ በተባለበት ቦታ የሚጎረፈውን ሕዝብ መመልከት ነው፡፡ በተቃራኒው የልዑል አምላክ ኃይል መገለጫዎች እንደ ኋላ ቀርነት ሞኝነት ሲቆጠሩ በትልልቅ መንፈሳዊያን በተባሉ ሰዎች ሳይቀር ይታያል፡፡ ነገሩ አይፈረድብንም መተት እንጂ የእግዚአበሔር ሥም ኃይል እንደሚሰራ መቼ በልባችን እናምናለንና የቱንም ያህል በአፋችን ኃይል የእግዚአበሔር ነው እያልን ብንቀሳፍትም፡፡ ይህ ሕዝብ በከንፈሩ የእርግማን ዘሮች!

ያመልከኛል… የሚለው የአምላክ ቃል በትክክልም ለእኛ እንደሆነ እናስተውል፡፡ እኮ ኃይል የእግዚአበሔር እንደሆነ ካመንን ለሚያምን ሁሉ ይሆንለታል ይላል፡፡ እንኳን ሁሉ ሊሆንልን እንቆጣጠረዋለን የምንለው ሁሉ ሲጠፋብን ነው የሚታየው፡፡ ችግሩ የእኛ ማመን ነው ወይስ የአምላክ ኃይል አለመኖር????? ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ፡፡ ያመንን የመሰለን ሁሉ ተሸውደን የምድሩስ የምድር ነው የገሃነም እራት እንዳንሆን፡፡ ዳሩ ገሃንም (የዘላለም እሳት!!!) እንዳለስ ብናምን መች እንዲህ እንሆናለን፡፡ አለማመናችን በእናምናለን ድፍንነታችን መሸፈኑ ደግሞ አደጋው የከፋ ነው፡፡ አለማመኔን አርዳው (ቃሉ በወንጌል ማርቆስ 9፡ 23-24 አንድ ሰው ወደ ጌታ ቀርቦ ልጁን እንዲፈውስለት ቢቻልህ እዘንልኝ ባለው ጊዜ ጌታ ብቻልህ ትለኛለህ? ለሚያምን ሁሉ ይቻላል ባለው ጊዜ ሰውየው ደንግጦ ጌታ ሆይ አለማመኔን እርዳው ያለው ትዝ ስላለኝ ነው) ለማለት አንኳን እድል አላገኘንምና፡፡
አንዳንዶቻችን ራሳችንን መደለላችን እንኳን ሳይታወቀን አይተን እንድናምን የእግዚአበሔር ኃይል ሲገለጥልን እንኳን በምልክት አናምንም በሚል የራሱ በውስጣችን ያለው የክፉ መንፈስ ስልታዊ ሴራ እንዳናምን ተዳፍኖብን እንቀራለን፡፡ በእግዚአበሔር ተዓምር ማመን ምኑ ነው ጥፋቱ፡፡ ምልክትን ሁል ጊዜ ግን መከተል እንደሌለብንና ከእግዚአበሔር ያልሆኑ ምልክቶች እንዳያሳስቱን ምልክትን በጥንቃቄ እንድናስተውል ተነገረን እንጂ የልዑል አምላክ ኃይል ሲገለጥ ምልክት ነው እያልን እንድናወግዝ ልባችንንም እንድናደነድን አይደለም፡፡ በትክክልም እግዚአበሔር አምላክ ድሮ (እኛን ተረት እንደሚመስለን ሳይሆን) እንደሚያደርገው ዛሬም ያደርጋል፡፡ በትክክልም እሱን በሚያመለኩት ላይ ኃይሉን ይገልጣል፡፡ ችግሩ የልዑል አምላክ እግዚአበሔር ተዐምር ሳይሆን ምልክቱ እንዲገለፅበት ፀጋው የተሰጠውን ሰው ጭራሽ ተሰባሪና ሰው መሆኑን ዘንግተን የእሱ አምላኪ ስንሆን ነው፡፡ አደጋው ለባለፀጋውም ለእኛም ነው፡፡ ፀጋው በትክክል ከልዑል አምላክ ቢሆንም የሰዎች ሰውየውን ማድነቅና (ማክበር ግን አይደለም) ፈተና በመሆን ትመክህት እንዲያድርበት ሆኖ በመጨረሻ እሱም የተከተሉትም በአሰከፊ ሁኔታ መጥፋታቸው ነው፡፡ ትምክህታችውን ለልዑል አምላክ ክብር መገለጫ የሰጡ ግን ምንም አይሆኑም፡፡ ከላይ የጠቀስንውን የቅዱስ ጳውሎስን ታሪክ ማስተዋል ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ ትምክህቱ በልዑል አምላክ እግዚአበሔር ነበርና፡፡ በድፍረትም እኔ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተ እኔን ምሰሉ እንዳለም፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ንግግር ከስጋዊ ትመክህት አልነበረም በአምላክ ዘንድ ያለውን መተማመንና ለእምነቱም ያለውን ቁርጠኝነት ለሌሎችም ለማሳየት እንጂ፡፡

የምንገርመው ግን የእግዚአበሔር ሲሆን በምልክት አናምንም ያለንው የሰይጣንና አጋንንት ሥራዎች በሆኑት ምትሃቶች (ማጂክ) ስናምን አለማፈራችን ነው፡፡ ኧረ አንዳንዴም ሳይነሳዊ ትንታኔም ለመስጠት እንሞክራለን! እስኪ በየ ጋዜጣው/መጽሔቱ ላይ ያሉ የአስትሮሎጂ (የእድል ጥንቆላዎች)፣የኦሾና ራምፓ፣ የመዳፍ መስመር የመሳሰሉትን ስናነብ ምን እያደረግን እንደሆነ እራሳችንን እንታዘብ፡፡ በየጠንቋዩና ቃልቻው ቤት ለሚደረጉ የሰይጣን ምልክቶችስ፡፡ በአንድ ወቅት ዛሬ በማረሚያ ቤት ያለው ሰው በጣም ብዙና እጅግ ትልቅ የተባሉ ሳይቀሩ ተከታዮቹ እንደሆኑ ያወቅንው ኋላ ነው፡፡ የሰውም ብዛት ሲታይ ምን ያህሉ ሰው እውን እግዚአበሔርን እያመለከ እንደሆነ ጥያቄ ውስጥ የጣለ ነው፡፡ አንዳንዶች የሌሎችን ገንዘብ ፍለጋ (ለመሰለብ) ወይም ሌላውን ለማጥፋት በመቶ ሺዎች ገብረዋል፡፡ የክፉ ሰው ዘሮች! እነዘህ ክፋቶች እንደሚሆኑልን ስለምናምን በመቶ ሺዎች እንገብራለን፡፡ የእግዚአብሔርን ኃይል ግን ለማስተዋል አእምሮአችን ተዘግቶብናል፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ አልፈለግንምና፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ይላልና፡፡

አምላክ ሆይ ለማይረባ አእመሮ አሳልፈህ አትስጠን! እናስተውል ዘንድ አቤቱ አእሚሯችንን ክፈት! እርግማናችንንም አስወግድ! አሜን!

Who is priest/Exorcist Memeher Girma Wondimu?

 

የቀድሞው የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም ዘላለም እሰይ ስለ መምህር ግርማ ምን ይላሉ? 

 

 

What are the views of Ethiopian Orthodox Church on Memehir Girma Wondimu and his healing services?



 

Interview of Memehir Girma with radio Abysinia on leb le leb program

This is 4 part interview with Memehir Girma on radio Abyssinia. He has a message for Ethiopian diaspora. Memehir Girma clarifies everything he does and delivers a strong message on how to identify and remove the influence of evil spirit effects on family and life. He gives his contact address, mobile with precise instruction on how and when to contact Memehir Grima.  This is a must listen!!


Part 1 & 2


PART 3 CLICK here!



From memihir Girma VCD-

Nequ part 12 

In this video you see evidence that Memehir Grima is given the rank of gospel preacher on September 23,  1985 E.C. considering his long services. Along with this various other certificates showing his ability to heal and preach are presented. These are then followed by a ceremony honoring the services of Memehir Girma. It is opened by administrator of saint Estifanos church. Memehir girma is honored for his true healing services, preaching and contribution to the development of the church. The following are particularly mentioned: his 35yrs work that converted and brought back many followers to the church, he has helped many be free of bad spirits, claim back their spiritual life up to the holy Eucharist among others. The testimony of many church fathers follows, approving the he is the real father.

 

Nequ part 16

In Addis Admas news and others you may have read that memehir Girma service has been banned. In this part you see that he has been given the permission to continue his services after it has been proved by ETOC patriarchate head office on November 10,2004 E.C that his healing services are real. 

From cnn ireport. Please see this report in Part 15A too.

 http://ireport.cnn.com/docs/DOC-627906

Thousands of Ethiopians, foreigners find healing in Addis Abeba

Priest/Exorcist Girma Wondimu
The head priest/exorcist has advice
28-6-2011
By Tedla T.

Thousands of Ethiopians and some foreigners head to two Churches in Addis Abeba looking for religious healings from an Orthodox Priest/Exorcist Girma Wondimu. On Saturday and Sunday to St. Stephen Church, Meskel Square and on Tuesday and Wednesday to St. Michael Church, in Merkato, Addis Abeba. Thousands of Ethiopians and foreigners have given testimonies of healing and many have been open-mouthed by the miracles they have witnessed. Almost all types of ailments are healed through ‘Faith Healing’. This is one of the talking points in the religiously strong Addis Abeba today. The Priest regularly gives religious teachings and healing through baptismal and exorcism in the Ethiopian Orthodox Christian ways. I have had the opportunity to speak to him.
The excerpt follows,

Tell me about yourself please?

Priest/Exorcist Girma: I was born in 1951 (Ethiopian Calendar) in Bale, Ethiopia. In 1962(Eth.Calander) , I was ordained a deacon by Abune Mekarios at the St. Michael Church, in Bale Goba . I served as a deacon for 15 years in different parishes in Bale, Ethiopia. Then I completed preaching and prayer courses. Recently I was given additional trainings on prayers by religious fathers. They strengthened me. By taking the Holy Eucharist (Communion) often, I also got the spiritual gift from God that enables me identify the spirit. When teaching the Gospel to the people attending worship, I was then able to identify where the spirits were  amongst worshipers. When you take the Holy Communion, you see what Jesus Christ had seen. You do what Jesus Christ did. Because He said in the Gospel of John 14:12 “Very truly I tell you, whoever believes in me will do the works I have been doing, and they will do even greater things than these, because I am going to the Father.” In this world where betrayal is much, God is out of the philosophy; to quieten the material world’s wealth and wisdom, and reveal the secret; he showed/gave me the opportunity through His gift. So now I can say I have a Doctorate Degree of 35 years of investigation and research on spirits. And in all those years, I had served in Bale Goba, Zeway, Butajira (many Pentecostals and Muslims have been converted to Christianity),Meki,Jima,Teppi,Yirga Cheffe, Sidamo, Harar, Somali region, Neeus Tabia Ketema, Sudan, I have been in Addis Abeba for the past good years and will soon be heading to Wello, Haik, and others.

What did it include, prayers only or did it include healing and other services as I watched in the series of the Video CDs of the Faith Healings you have released?

Priest/Exorcist Girma : What you watched on the Video CDs is just a tip of it. Through my Service, all kinds of healing, safety and deliverance works are done. I spent all the 35 years in this Service. Out of the 35 years, I spent  nine of them exiled in Sudan.

Do you have a family?

Priest/Exorcist Girma : I am married and have three children. I live with my family now.

Doing these time and space taking Faith Healing Services and being over crowded with such a large mass, Won’t this affect your private and family life?

Priest/Exorcist Girma : My private life is only for prayer. The rest would all be fulfilled by the Will of God. After my Faith Healing programs, I spend my time in prayers and taking the Holy Communion frequently, because the way to defend devil is when you have Lord inside you, so it is by taking the Holy Communion that the devil is won and you get strengthened. Because He said “I am the bread of life.’’

Can you list me the total number of healings and their types?

Priest/Exorcist Girma: They are so many . Because it is quite expensive to have the blank CDs we use for recording the films on, we only do recordings sometimes and only few of the miracles selected. Hundreds of people are healed every day. For instance in Somali region, Ethiopia, we used to heal a bunch of 20 to 40 people at a time. So it is difficult to put it in figures but you can say around a million. You can say almost half of the 80 million of our population has been affected by demons. You can say after the revolution (1974), Habessha has become devil.
There were many types of cures ;some whose tongues was inside their necks were healed , crippled, disabled, deaf and some who were in coma were also healed, scientists were also cured, infertile gave birth , Pentecostal spirits were also healed . Many Europeans and Americans have been healed here too. Some of them are in high positions in their own countries. Their demons are easy to exorcise because it is not worshiped unlike ours.
I know that most priests in the old days used to have the gift of Faith Healing. Especially those that were before the coming of modern schooling were able to heal. Then, those who have abused their religious education for their own and devil’s benefits have popped up, who are wrongly named, Debteras (evil doers).


To those of my fellows in my generation who believe in rationality and logic such cures and miracles are unacceptable, some would even laugh when told about the miracles. What is your message for these people?


Priest/Exorcist Girma: These people are of four types: those that have totally denied God and are possessed by demon, second are relatives of the devil (witches, shamans, evil eyes and son ), third those affected by the spirit of philosophy (these is the modern Satan, say as in the case of Marxist and similar laws), fourth are those who succeed the place of devil by having a behaviour of discriminating, hate, and love of riches . The last or the fifth group are Christians. The four believe in materials. They believe in philosophies and when they see miracles they happen to be scared or at other times continue with their denials.


Such services of “Faith Healing’’ in our Church are increasing. I have seen many cases in Addis Abeba in places like Piassa, Ferensayee and so on. Some were proved wrong. How do you see that?


Priest/Exorcist Girma: Gifts of God's generosity are different. As long as one can heal, opposes the devil, and the rules and regulations of the Church are respected, I wouldn’t have anything against it. I believe the gift is only from God.


Did you have bad experiences?


Priest/Exorcist Girma: I was labelled by some laity as a non Christian and was even unable to find a place to sleep for some time. Some had also said that I don’t eat food at all. When I said that my time to break my fast has reached, an elderly lady whose children have been healed once said to me “do you also eat?” I also heard that some people accused me of being a magician, using a Sudanese witchcraft. Those who have been doing this were the types of people I sectioned into four above . One of the saddening things is that priests that knew me very well also failed to testify about me due to jealousy and bad intentions. Some with a rank of Pope, whom I had known in person, had also sent out a rumour, stating that I had a Sudanese witchcraft to do all these healings and this, had stereotyped many worshipers. This shows that the spirits of jealousy and badness that were in there during Genesis had not yet left the Church. There were also intimidations, breaking of my water pipe, protests and so on. But this is all improving now. Worshipers have known the truth now.


They say treasury gifts can spoil …do u take gifts?

Priest/Exorcist Girma: For all these services, nobody pays. It is all free. And there is no precondition to be healed all human beings of all religions, race or identity are allowed to come for healing. They get all the services for free.


So how do you live? Any source of income?

Priest/Exorcist Girma: From the sale of the Video CDs. The CDs show some of the live recorded miraculous ‘Faith Healing’ programs and preaching.

 

Do you have message for Ethiopians? We Ethiopians are suffering and agonized both in Ethiopia or while in exile. Our problems seem to be endless. Though we were one of the grandest, now we are the helpless.


Priest/Exorcist Girma : Very good. We are in this alarming image for one thing because our ‘Ethiopianess’ has gone out of us. Secondly, our religious direction has been contaminated by the communist thinking. Thirdly, a cursing spirit has entered us and our leaders have built the generation repeating the ‘Destroy it!’’ slogan. There was this culture that promoted the destruction of our past history, the Church, the monuments, and the heroes who protected the country. I am not a politician but I think a child that grew up with those slogans of ‘destroy it’ couldn’t be able to have love for the Country and values and respect for a religion. So we are harvesting a generation that grew up with the ‘destroy it’ slogan/word. That is why whatever we work and our fruits are destroyed, we are exiled and there is destruction there too, here we are and it is destroyed too, it is all destruction. Why? Because what we sow was curse, so we reap curse too. Ethical morality has been broken by Marxist thinking too. Sixty thousand Ethiopians in the times of the Revolution were always marching on Sundays saying “destroy it”, they used to eat meat on Wednesday and Friday that was a time where there was extreme exaltation and indulgence .When their slogan was made a reality by God, it is destruction again. The other thing is that , “going 40 years forward and 40 years backward’’ has become one of the natures of the Ethiopian history.


What is the solution?


Priest/Exorcist Girma : We have to return backward meaning to prayers, ethical education, the religious martyrdom of our fathers, firmness in belief, ceasing lying, and fearing God. Ethiopians have to begin a life of sainthood/sanctification. Sanctified people won’t starve, go to war, migrate, because God is the worrier under the protection of Angeles, they will be victorious. We aren’t sanctified. So all of us have to be blessed. If all are blessed, they will always win.

People of the world had attempted to change the world with materials but material is only reducing human beings. We see the technologies, satellites, internet, and mobiles advancing…although it is good and useful; it is also passing its limit. Leaders have been very wrong. Politicians have extremely lost their direction. So unless we return to the One who shows us directions, we will be in complete darkness. If we return to God, what we Ethiopians have is enough to the world. We are not either with the West or with ourselves; we have become losers.

In short, I would like to say to Ethiopians from the youth to elders to stop being lured with little things for the sake of filling their belly and be firm on their faith.