Tuesday, December 27, 2016

በሻሌ ንቡ ቅ/ሚካኤል - Video

ዋካ ቅድስ ጊዮርጊስ ገዳም

በ15ክ/ዘመን የተመሰረተው አብነ ጵጥሮስ የቀደሱበት የባረኩት በደመና የመጣ ታቦት ቀድሞ ከ15ክ/ዘመን በፊት/ መንዝ ዋካየአብይ ገብረመንፈስቅድስ ገዳም/ ሲሆን 15ክ/ዘመን ላይ ዋካ ቅድስ ጊዮርጊስ ገዳም ተብላል፡፡በጣም ስለት ሰሚ ነው፡ጣልያን በወረረን ግዜ ቦንብ ጥለው ቤተክርስቲያኑን ሊያቃጥሉ ቢወረወሩ ቤተክርስቲያኑ አልቃጠል ሲላቸው ሰውን ፡ካህኑን እየገደሉ ቤተክርስቲያኑ አልቃጠል ሲላቸው የታቦቱን መጎናጸፍፊያ ለብሰው ሲሂድ ከዋካ ከቦታ አልፈው ሂደው ጉርሙኝ ቆላውየ4ሰዓት መንገድ ልብሱን ለብሶ ለብሰው ጣሊያኖቹ ሲሂድየአካባቢው ሰው /አቶ ተገኝ/የሚባሉ ሰው ይህ በምታዩት ጋሻ በመከት ጣሊያኖቹን በመግደልና ገደል በመክተት የጊዮርጊስ መጎናጸፊያ አስመልሰው መጎናጸፊያው(ልብሱ ):በዋካ ጊዮርጊስ ይገኝል፡፡

 




አቶ ተገኝ ጀግና ተብለው የደጃዝማች መሀረግ ሲሰጣቸው ቁረብ ሰጋወ ደሙ ተቀበሉ ሲላቸው በመንዝ አካበቢ ጀግና ሲሞት ቀረርቶ ;ይሸለላል;ይፎከራል ይህ ሳይደረግ ጀግና አይቀበርም፡፡እና አቶ ተገኝ ቁረብ ሲባሉ እኔን ጊዮርጊሰ ጀግና አርጎ ጠላቱን ገድይ ልብሱን አስመልሻለሁ እና ቁርባኑን ሰጋ ደሙን ጊዮርጊሰ ያቀዋል፡ሳይሸለልልኝ ሳይፋከርልኝ ብለው በ110አመታቸው ሞቱ፡፡ የሚገርሙአባት ናቸው በጀግና አሟሟትየተፋከረ፡እየተሸለለ በጀግና አቀባበር በ110አመታቸው አርፈዋል፡፡ስለት ሰሚው ዋካ ጊዮርጊስ የዱሮው ቤተክርስቲያንሳይፈርስ ሌላ ቤተክርስቲያን በመሰራት ላይ ሲሆን መርዳት ለእግዚአብሔር ማበደር ሲሆን ስለት ሰሚውን ዋካን በምንችለው አቅም እንርዳ የቤተክርስቲያኗ መሰረቱ በመሠራት በመውጣት ላይ ነው፡፡በረከቱ በያለንበት ከጊዮርጊሰ ይደርብን፡፡አሜን
ቦታው-+መንዝ ዘብር ገብርኤል ከአ/አ 260ኪሜ ሲሆን ከዘብር የ4ሰዓት መንገድ ሲሆን 4wdመኪና ቦታው ድረስ ይገባል ሜዳ ቀላል መንገድ ነው፡፡

Sunday, November 27, 2016

በራእይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገኝ የታየው ታቦት ተገኘ

ቅ/ሚካኤል ሚዛንና ሰይፍ ይዞ በዩኒቨርሲቲው ፩ኛ በር በኩል እየወሰደ ያሳየኛል፡፡”
/ታቦቱ መኖሩን የጠቆሙት ባለራእዩ ባሕታዊ በለጠ ዘነበ/
*                    *                    *
aau-st-michael-ark
 
(አዲስ አድማስ፤ ዓለማየሁ አንበሴ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፭፻፹፤ ቅዳሜ፣ ኅዳር ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ ሙዝየም ውስጥ፣ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ ታቦት የተገኘ ሲኾን፤ ታቦቱ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደተመለሰ ታውቋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ግቢ ታቦት ስለመኖሩ፣ “ራእይ ታይቶኛል” የሚሉ ባሕታዊ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ባስታወቁት መሠረት፣ ጥናት ተደርጎ መኖሩ በመረጋገጡ፤ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ብዙ ድርድር ከተደረገ በኋላ፣ ኅዳር 10 ቀን 2009 ዓ.ም.፣ ታቦቱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት መመለሱን በጉዳዩ ተሳታፊ የነበሩት መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አሣመረአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
“ታቦቱ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ጥያቄ እንደተቀረፀና የቅዱስ ሚካኤል ታቦት መኾኑን የሚገልጽ ማስታወሻ ተገኝቷል፡፡ ታቦቱ ከ68 ዓመት በላይ ዕድሜ እንዳለውም ታውቋል፤” ብለዋል – መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፡፡
ታቦቱ በዩኒቨርሲቲው ስለመኖሩ፣ ባሕታዊ በለጠ ዘነበ የተባሉ በራእይ ታይቶኛል በሚል በተደጋጋሚ ሲናገሩ እንደነበር የጠቆሙት መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፤ “ቅዱስ ሚካኤል ሚዛንና ሰይፍ ይዞ በዩኒቨርሲቲው ካምፓስ አንደኛ በር በኩል እየወሰደ ያሳየኛል፤” እያሉ ይናገሩ እንደነበርና፣ ይህንንም በ2003 ዓ.ም. አካባቢ ለፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ መግለጻቸውን፤ ነገር ግን ትኩረት የሚሰጣቸው ሳያገኙ መቅረታቸውን ያስታውሳሉ፡፡

ባሕታዊው፣ በ2007 ዓ.ም. ይህንኑ ራእይ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ማሳወቃቸውንና የሚመለከታቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሥራ ሓላፊዎች ጉዳዩ እንዲጠና ማዘዛቸውን መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አውስተው፣ በጥናቱም ጽላቱ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መኖሩ መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ታቦቱ ለቤተ ክርስቲያንዋ እንዲመለስ ከዩኒቨርስቲው ጋር በርካታ የደብዳቤ ልውወጦች ተደርገዋል፡፡
መጀመሪያ ላይ ዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ተቋም እንደመኾኑ፣ ቅርሶችን ተከባክቦ የመያዝና ለትውልድ የማስተላለፍ ሓላፊነት እንዳለበት በመግለጽ፣ ታቦቱን ለቤተ ክርስቲያንዋ ለመመለስ በእጅጉ ተቸግሮ ነበር፤ ይላሉ መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፡፡ ኾኖም ጽላት ለቱሪስቶች(ለጉብኝት) ክፍት ኾኖ መታየት የሌለበት የሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያና  መግለጫ በመኾኑ፣ በዩኒቨርሲቲው ሙዝየም ውስጥ ቢቀመጥ ትርጉም እንደሌለው ስምምነት ላይ በመደረሱ፣ የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን በአደራ ተረክቦ እንዲያስቀምጥ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ታቦቱ፣ አልተረስቶን በሚል ስያሜ፣ በመዝገብ ቁጥር 1761 ተመዝግቦ የተገኘ ሲኾን፣ ሚስተር ስቴፈን ራይት በተባለ ሰው፣ እ.አ.አ ሰኔ 12 ቀን 1961 ወደ ሙዝየም መግባቱን መጋቤ ምሥጢር ይናገራሉ፡፡ ነገሥታት ታቦት አስቀርፀው በቤተ መንግሥታቸው በሚገኙ አብያተ ጸሎታት(ሥዕል ቤቶች) የማስቀመጥ ልምድ እንደነበራቸው የጠቀሱት መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፤ ምናልባትም ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ይህን የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ሳያስቀርፁት እንዳልቀረ ግምት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ “ታቦቱ በዩኒቨርሲቲው ሙዝየም 3ኛ ምድር ቤት ውስጥ ለብቻው በተሠራ ቤት ውስጥ ተደብቆ ነው የተገኘው፤ የሙዝየሙ ሠራተኞች እንኳን ታቦት መኖሩን አያውቁም ነበር፤” ብለዋል መጋቤ ምሥጢሩ፡፡
ከሰኔ 12 ቀን ጀምሮ፣ ከመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ጋር ይገናኙ እንደነበር የገለጹት ባለራእዩ ባሕታዊ በለጠ ዘነበ፣ በተደጋጋሚ ወደ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት እየሔዱ ቢናገሩም ትኩረት አለማግኘታቸውን ጠቅሰው፣ በኋላ የቤተ ክርስቲያኒቱ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንና የቤተ መዛግብትና ቅርስ ክፍል ሓላፊዎች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ታቦቱን ከዩኒቨርስቲው ለመረከብ መቻሉን ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር የኾኑትን ፕ/ር አሕመድ ዘካርያን ስለ ጉዳዩ ጠይቀናቸው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይኾኑ ቀርተዋል – “አኹን ብዙም የምገልጸው ነገር የለም፤” በማለት፡፡
the-imperial-genete-leul-palace-and-menbere-leul-st-mark-church
የቀድሞው ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት(የአኹኑ የአ.አ.ዩ. የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም – በግራ) 
እና የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን(በቀኝ)
በዩኒቨርሲቲው ሙዝየም የተገኘውን የቅዱስ ሚካኤል ታቦት አስመልክቶ፣ ለብዙኃን መገናኛ እና ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ፣ ለጥር 8 ቀን 2009 ዓ.ም. መርሐ ግብር መያዙን መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አስታውቀዋል፡፡
አኹን በ6 ኪሎ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ፣ የግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት የነበረ ሲኾን፣ ታቦቱን በአደራ የተረከበው የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም፣ የንጉሠ ነገሥቱና ቤተሰቦቻቸው ሥዕል ቤት(ጸሎት ቤት) ኾኖ ያገለገለ ነው፡፡ የ1953 ዓ.ም. መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የንጉሡ ቤተ መንግሥት ወደ ኢዮቤልዩ በመዛወሩ፣ የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥትን ለትምህርት ተቋምነት በስጦታ አበርክተዋል፤ ጸሎት ቤት የነበረው የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ኾኗል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ: ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ ታቦተ ቅዱስ ሚካኤል ተገኘ

የቅዱስ ገብርኤል ጽላት በአንድ አባት ራእይ ተገኘ

Tuesday, November 15, 2016

የእመቤታችን የቤት እቃዎች በግብጽ

እመቤታችን በግብፅ ውስጥ በነበረችበት ወቅት ልጅዋን ኢየሱስ ክርስቶስን ሦስት አመት ከስድስት ወር ከ10 ቀን ሲሆን  እመቤታችን በወቅቱ ትገለገልበት የነበረው ሙቀጫዋ ፣ድስቷ እንዲሁም: ጌታችንን ገላዉን ልብሱን ታጣጥብበት የነበረዉ ከዲንጋይ የተሰራ መገልገያ ዕቃዎችዋ ሲሆን ይህን ቅዱስ ስፍራ ለማየት የታደሉት ምዕመናን ጭምር ደስታቸውን በእልልታ ና በዝማሬ በድምቀት እያከበሩት ይገኛል።

Wednesday, September 21, 2016

የቅድስት አርሴማ አዲስ ፀበል


አዲስ የፈለቀ ታላቅ የፀበል ፈውስ ስፍራ ኑ እና የእግዚአብሔር ድንቅ ስራውን መስክሩ::

ቸው ቅዱሳን ስም የሰጠንን ታላቁን የፀበል ፈውስ ነው፡፡ ቅዱስ ፀበል አፍልቆ ህዝቡን እየባረከና እየፈወሰ ይገኛል፡፡ አንከሶች መርገጥ (ቆመው መሄድ) ችለዋል እጃቸው የተቆለፈ ሽባዎች እጃቸው ተፈቶላቸዋል በአልጋ የመጡ ተፈውሰው በእግራቸው ሄደዋል በውስጥ ደዌ የሚሰቃዩ ፈውስ አግኝተዋል እባብ፣ አባጨጓሬ እና ወስፋት ከሆዳቸው ፀበሉን በመጠጣት ወጥቷል፡፡ ከኤች አይ ቪ ኤድስ ከትቪ በሽታ የተፈወሱ ሰዎች አሉ ከአኪንታሮት በሽታ የተፈወሱ ሰዎች አሉ
ፀጋ እ/ር በባዛላቸው በመላው ኢትዮጲያ ባገለገሉ አባት ታግዞ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች በቅድስት አርሴማ ፀበል ከቁስል ነገር ድነዋል፡፡ 





ካነበቡት በኋላ እባክሆን በፍጥነት መልክቱን በማጋራት ለሌሎች መዳን ምክንያት ይሁኑ፡፡
አድራሻ ከ ከዊንጌት አደባባይ ተሻግራቸው ወደ ሙለጌታ አባት መናፈሻ በሚወሰደወ መንገደ ከደረሱ ሰዉቸነ መጠየቅ ይቻላል ለበለጠ መረጃ
0910792943(አባ ዜና) 

0913986208 ወይም 
0920146348.
የሰማእቷ እናታችን ረድኤል በረከት ይደርብን አሜን::

Sunday, August 14, 2016

ተዕምረኛ ድንጋዪች በዳጋ እሥጢፋኖስ

አቡነ ኂሩተ አምላክ ሁለት ድንጋዮችን በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ጣና ባሕርን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተዋል፡፡ ጻድቁ የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ ‹‹ዓቃቤ ሰዓት›› እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ በጽኑ ተጋድሎ ኖረው ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው በዛሬዋ ዕለት ነሐሴ 8 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ በረከታቸው ይደርብን፡፡


Wednesday, August 10, 2016

ጎንድ ተክለ ሐይማኖት ገዳም

ጎንድ ተክለ ሐይማኖት ገዳም ከአማራ ክልል ርእሰ መዲና ባህር ዳር ተነስተን ዘንዘሊማ ሐሙሲት ከዚያም የፎገሮቹን አገር ወረታን እያቆራረጥን አዲስ ዘመን እንደደረስን የጎንደሩን መስመር ተከትለን የጻድቋን እናት ጣራ ገዳም ደንን እያማተርን በውብ የአእዋፍ ዜማ ተደምመን ከተቻለ መኪናችን ቆም አድርገን ሰላም ለኪ ብለን በአጸዶቿ መአዛ ህሊናችን ሰብስበን ጉዟችን አሁንም ወደፊት ስንቀጥል የሊቦ ከምከምና የጎንደር ዙሪያ ወረዳ መካለያ የሆነችውን በ'ራሷ ጊዜ መድመቅና ከተሜነት የጀመረችው ሰንደባ ወንዟን አርኖን ተንተርሳ ውብ የሆነውን አየሯን እየለገሰች ትጠብቃለች ወንዟ አርኖ አመቱን ሁሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለአርሶ በሌው ውሐውን ይለግሳል አርሶ አደሩም የተለያዩ ምርቶችን እያመረተ ሲያሻው ወደአዲስ ዘመን ያልያ ወደእንፍራዝ በትናንሽ ታክሲዎች እያጓጓዘ ለከተማው ማህበረሰብ ይቀልባል። አርኖ የባለፉት ወራሪዎቻችን የጣሊያን ሰዎች ስያሜውን እንደሰጡት ይናገራል። ከ'ዚህች ትንሽየ የገጠር ከተማ እልፍ እንዳሉ በቅርብ ርቀት ጋርኖን ተንተርሳ እንፍራዝን ታገኟታላችሁ፡፡ እንፍራዝ ቀደምት ከተማ ስትሆን ከ'ሷ በቅርብ ርቀት የደብሳን ግንብ የጉዛራ ቤተ መንግስት አጼ ሰርጸ ድንግል በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የከተመበት እንደነበር ታሪክ በየድርሳኑ ይዘግባል። ከዚህም ጋር በተገናኜ እንፍራዝ የአጼ ቴዎድሮስ እናት ርስት ቦታ ስትሆን ተወላጅነታቸውም 'ዚህች ከተማ አካባቢ እንደነበረ የታሪክ ዘካሪዎች በየጦማራቸው ከትበውታል፡፡

እንፍራዝ ፍቅር ተዘርቶ የበቀለባት ትንሽ ቦታ ግን ማህበረሰቦቿ ተቻችለውና ተረዳድተው የሚኖርባት ከደረቅ ወደብ ተነስተው የሚመጡ ተሳቢ መኪኖች ጎንደር በር ጣዕመት ወደባህርዳር መውጫ አልሚ ምግብ ቤት እረፍት አድርገው ያሻቸውን በልተው ጠጥተው ይጓዛሉ። ትናንሽ ህጻናት ቆሏቸውን በሰፌድ ብትን አድርገው ይውሰዱ ይብሉ እያሉ በውብ ፈገግታቸው ራብን አፈ ድሜ ያበሉታል። እንዳልኩት እንፍራዝ ካረፉ በኋላ ጉዞዎን እንደቀጠሉ ቁልቋል በር ላይ የሰፈሩትን የወረኢሉ ሙስሊሞች ወሎ ያለን እስኪመስለን ድረስ "ዴ " ን አጥበቀው እየጠሩ በፈገግታ ያስዋኛሉ። መኪና ላይ አያጧቸውም ተሳፍረው አብረው ካገኟቸው እንዴት ከወረኢሉ እንደመጡ 'ዚህ አካባቢ ሰፍረው እንደቀሩና ተላምደው በፍቅር እየኖሩ እንዳሉ በሚያምረው ልሳናቸው ይተርካሉ፡፡ " በል አቦ ጃል ዴርሻለሁ ወገን" ብለው ዳገታማውን ጉዞ ይያያዙታል። ቁልቋል በርን እንደጨረሱ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ርእሰ መዲና ማክሰኝትን ያገኛሉ።

ከዚህን በኋላ መኪና ካልያዙ ወርደው የደጎማ ታክሲ ያልያ አውቶብስ ያገኛሉ።  ጉዞዎን ከጎንደርም የመጣ ይሁን ከባህርዳር ጅማሬው ከተማዋ ላይ ነው፡፡ ከከተማዋ 3 ኪሎሜትር በላይ ከተጓዙ በኋላ የአርባያውን መገንጠያ ያገኛሉ። ይህ መነሻ ወደተነሳንበት ጎንድ ተክለ ሐይማኖት ገዳም ይወስደናል፡፡ ከጎንደርም ከባህርዳርም የመጣ ተጓዥ ከአስፓልት ወጥቶ የጠጠር ጎዳናውን ይያዙታል፡፡ 

ከ'ዚህ መነሻ አስፓልት ተነስተን ጎንድ ለመድረስ 24 ኪሜ አካባቢ የሚርቅ ሲሆን መንገዱን እየተንገራገጩ መጓዝ የግድ ይላል።
ደጎላን ዳስንና ድንዛዝን ከታለፈ በኋላ አስራ ዘጠኝ ሐያ ኪሎ ሜትር እንደተጓዙ የኢብን ኢብራሂም አልቃዚ ( ግራኝ እጁ ) የሞተበትን ስፍራ ያገኛሉ። ይህ ቦታ የፖርቱጋል ወታደሮችን መርቶ የመጣው ክርስቶፎር ደጋማ (የመርከበኛው የቫስኮ ደጋማ ልጅ ) ቱርኮች ቀይ ባህር ቢገሉትም ተተኪው የነበረው በርተለሚዎዝ ዲያዝ የንግስቲቱን ሰብለ ወንጌል ልጅ የአባቱን የልብነ ድንግልን መንበረ ስልጣን እንዲመልስ ከፍተኛ ጉትጎታ ታደርግ ነበርና ክርስቲያኖቹ ፖርቱጋሎች አግዘውት ከ'ዚህ ስፍራ ግራኝንና ተከታዮቻቸውን ድል አደረጉ። ግራኝ በኢትዮጵያ ታሪክ የቆየባቸው 15 አመታት የተረጋጉ አልነበሩም። መጨረሻውም በዚህ ስፍራ በሞት ተቋጭቷል። ያልተረጋጉ የጦርነት ውሎዎች በሟቹ ደጋማ ሰም ከተሰየመችው ከተማ ደጎማ በቅርብ ርቀት ሲከናወን ይህንን ስፍራ የአገሬው ሰዎች "የድል በር " ብለው ይጠሩታል፡፡ ተራራማው የድል በር ላይ ተሁኖ ፊት ለፊት ደጎማን ከበስተኋል አድርገን ስንመለከት ደንቀዝንና የበለሳን ፈፋዎችና የተራራ ሰንሰለቶች ያያሉ። በእውነት የኢትዮጵያዊነት ህብር የሚገለጽበት ስፍራ ወኔ የሚሰነቅበት ስፍራ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከምናብ ትውስታ በኋላ ወደፊት ሁለት ኪሎ ሜትር እንደተጓዙ ጎንዶችን ታገኛላችሁ። ይህ ስፍራ ወደ ከፍተኛ የተራራ ነጥብ መሄድዎትን ይነግርዎታል ጠንካራ ብርድ አለና ጃኬት መያዙዎትን ያረጋግጡ።
ጭራቆ ወንዝ ላይ እግረዎትን ተለቃልቀው ከፈለጉ ደጎማ አርፈው ቢወጡ ጥሩ ነው። ከአፍ የሚጣል አይጠፋምና ያልያ ግን መኪናዎን ደጎማ ትተው የጎንድ ተክለ ሐይማኖትን ገዳማ የእግር ጉዞ ይያያዙታል።

የአየሩ መአዛ ከሌሎች ገዳማት በላቀ ሁኔታ ይጠራዎታል። የቅዱሳኑ መአዛ አለማዊነትን ይደፍቃል በግምት ከተራራማው ክፍል ወደታችኛው የበለሳ ተዳፋት ይምዘገዘጋሉ። መንገዱን የገዳሙ መስራች አባት አባ ዮሐንስ ( ዘግብጽ ) ሲሆኑ እኝህ አባት ለበለሳ በረከት ናቸው። በስጋዊ የህይወት ዘመናቸው በለሳ የወተቱና የወገሚቱ የማሩና የቅቤውን ሁኔታ ስናስብ ልብን ቀስፎ ይይዛል። በጸሎታቸው ጸላኤን ረትተው ሊጥልባቸው የነበረውን የተራራ ናዳ ገስጸው አንጠልጥለውታል፡፡ ዛሬ ድረስ ናዳው ተንጠልጥሎ ይታያል። ከዚህም በላይ ደግሞ ሊያስታቸው የመጣን ጸላኤ አሰልጥነው መንገድና ዘመናዊ ሊባል የሚችል የመስኖ ካናል አሰርተውታል። መልሰው እንደገና በር ቆልፈው በአንዱ ዋሻ ዘግተውበታል።

አቡነ ዮሐንስ ዘግብጽ በረጅም ዘመናቸው በአካለ ስጋ እያሉ ለዚህ ገዳም ስርአት ሰርተው አልፈዋል። በኋላም ጻድቁ ተክለ ሐይማኖት በእንግድነት መጥተው ለጻድቁ ዮሐንስ ስርአተ ምንኩስናን ሰጥተዋል። የቆብ አባትም ጭምር ናቸው፡፡ ትውልድ በዘመን ጅረት ቢያልፍም ጎንድ ( ጉንደ ወይን) ከአስራ አንደኛው አስራ ሁለተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በቅድስና ኖሯል እኛ ደግ አባታችንም በአካለ ስጋ ለረጅም ጊዜ ቆይተዋል። ምንኩስና ሰርተው ህዝብን እየማለዱ ለትውልድ አስተላልፈዋል። ከ400 በላይ መነኮሳት በብህትውና ይኖሩበታል፡፡ እያንዳንዱ መነኩስና መነኮሳይት የተለየ ስፍራ አላቸው። ገዳሙ ሰፊ የሆነ ክልል ያለው ሲሆን መነኮሳቱ ጠንካራ የስራ ባህል ለማየት የሚፈልግ የየትኛውም ማህበረሰብ ክፍል ያለምንም እርዳታ በጾም በጸሎት በርትተው ደግሞ ለአንዲት ማእድ ሲሉ ሰርተው እንጅ ለምነው ያቆሙት ቤት የላቸውም። ነገረ ስራቸው ሁሉ ክርስትና ብቻ ነው የፊታቸው ጥንካሬ አለምን ድል ያደረጉበት ሰይፋቸው ጽናት ይሆናል። ጉንደ ወይን ባለፉት የታሪክ ዘውጋችን ስናነሳ ሲሲኒዮስ ካቶሊክን ሲቀበል  " ሲሲኒዮስ ይፍለስ ፋሲለደስ ይንገስ " ያሉት የጉንደ ወይን መነኮሳት ናቸው፡፡ ያሉትም አልቀረ ከደንቀዝ ቤተ መንግስት ተነስተው እስከ ላይማው ሰሜን ድረስ ደማቸውን አፍስሰዋል። (ደንቀዝ የአጼ ሲሲኒዮስ መናገሻ ከተማ የነበረች ሲሆን ከጎንድ በቅርብ ርቀት ትገኛለች፡፡) የገዳሙ መነኮሳት ከሌሎቹ ታላላቅ ገዳማት ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው፡፡ በገዳሙ ሁለት አብይት በአላት አሉ፡፡ ነሐሴ 24 የጻድቁ ተክለ ሐይማኖት እረፍት ይዘከራል። በዚህን ወቅት ከተለያዪ ስፍራዎች ተሳላሚዎች ይመጣሉ፡፡ መነኮሳቱ ለመጣው ተሳላሚ ሁሉ ምግብ ያቀርባሉ የማረፊያ ቦታ ያዘጋጃሉ።

ፍራፍሬው በቆሎው እሸቱ እንደልብ ነው። ጉንደ ወይን የተገኘው ሁሉ ይበላል። በሚገርም ሁኔታ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳላሚዎች መጥተው ንፍሮ ቅቅሉን ጠግበው በልተው ለጉዞ ስንቅ ይቋጥራሉ። ጠላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠመቀበት ስፍራ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡ ይህንን ጠላ ደግሞ የሚጠምቁት ወንዶቹ መነኮሳት ናቸው፡፡ ሌላው ከላይ የስራ ባህላቸው ለመነሻ ብጠቅስም መነኮሳቱ ወንዶቹ ያረሱት፥ አያርሙም ፥ ያረሙት አያጭዱም፥ ያጨዱት አይወቁም። ምርት የሚያጓጉዙት ሌሎች ናቸው፡፡ ስርአታቸው ሁሉ ህግ ነው። የሐይማኖታዊ ስርአቶቻችንን ዶግማና ቀኖና በጥብቅ አባታዊ ፍቅር ተምሮ ለመውጣት ጉንደ ወይን መምጣት።
የሚያምረውን ተፈጥሮአዊና ሐይማኖታዊ ስፍራ ይዩ በተጨማሪም በጸበሉ ፈውስን ያገኛሉና ጉንደ ወይን ይምጡ...

ድንቃ ድንቅ ገቢረ ተዐምራት በ ወይንዬ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወአቡነ ህጻን ሞዓ ገዳም


Tuesday, July 26, 2016

ድንቅ ተአምር በሽንቁሩ ቅድስ ሚካኤል

ዛሬ ኪዳነ ምህረት በእለተ ቀኗ በሽንቁሩ ቅድስ ሚካኤል ፅበል ስፍራ የተደረገ ድንቅ ተአምር .
የእግዚአብሔር ድንቅ ተአምር ለዓለም ይመስክሩ..!!!

እንደምን ከረማችሁ ወዳጆቼ ባለፈው የራሴን ታምር መስክሬላችሁ ነበር አሁን ደሞ እኔ ከተከራየሁበት ቤት አጠገብ የምትጠመቅ በ አለም ስሙዋ ወይዘሮ ማሬ የተባለች የ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ በ ሽንቁሩ ደብረ መድሀኒት ቅዱስ ሚካኤል ፀበል የተደረገላትን ድንቅ ታምር እንደዚ ትናገራለች ለዘመናት እግሩዋን እያስነከሰ በጣም ያሳምማት ነበር የምትሰራው የምግብ ስራ ስለነበር እሱዋ ግን እረጅም ሰአት የምትቆምበት ነበር የመሰላት ነገሩ ግን ወዲህ ነው በ ቅርብ በጓደኞችዋ የተሰራባት መተት ነበር ቆማ እንዳትሰራ እና እንደልብ እንዳትራመድ ነበር የተፈለገው ታድያ በ ቅዱስ ሚካኤል ምልጃ ፀበሉን ለ 4 ወር ስትጠመቅ ቆይታ ዛሬ በ16/11/2008 ዓ.ም ከ ቀኝ እግሩዋ ላይ አንድ ባለ ኮፍያ ሚስማር በ ስስ ላስቲክ ተጠቅልሎ ወጥቶላታል። የሚደንቀው ነገር ሚስማሩ ሲወጣ ምንም የህመም ስሜት አልነበረውም ደምም አልነበረውም እኔን የፈወሰ መላኩ ቅዱስ ሚካኤል እናንተንም ይርዳ ትላለች።
ወ/ሮ ማሬን ማግኘት እና መርዳት ለምትፈልጉ
+251920 34 3349 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
የቅዱስ ሚካኤል አምላክ ይክብር ይመስገን።
ይህን ድንቅ ተአምር ለአለም ይመስክሩ ዘንድ በቅዱስ ሚካኤል ስም እጠይቃለው።
Source: Memher Pawlos Melkea Selasie

Thursday, July 21, 2016

ማርያም ውቕሮ

ከአለት ተፈልፍለው ስለተሠሩ ውቅር ሕንፃዎች ሲነሳ ቀድመው የሚጠቀሱት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡ በ12ኛውና በ13ኛው ምታመት በንጉሡ ቅዱስ ላሊበላ ዘመንና ከርሱም በኋላ የታነፁት እነዚህ ውቅር ሕንፃዎች በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ናቸው፡፡ የእነዚህን ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የግንባታ ውርስ ከዘመነ አክሱም ትውፊት የቀጠለ እንደሆነ የሚመለከት ቢሆንም፣ በአንዳንዶች በኩል በውጭ ሰዎች እንደታነፁ የሚያመለክቱ አልታጡም፡፡ ሁለተኛውን አተያይ ተቀባይነት እንደሌለው ከሚጠቅሱትና ከዘመነ አክሱም የቀጠለ እንደሆነ አመላካቹ ከላሊበላዎቹ ውቅሮች 800 ዓመታት አስቀድሞ በትግራይና በዋግ ውስጥ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መገንባታቸው እንደሆነ ይወሳል፡፡
ከሃምሳ ዓመት በፊት በአዲስ አበባ (በሚያዝያ ወር 1958 ዓ.ም.) በተደረገው ሦስተኛው የኢትዮጵያ ባህልና ጥበብ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ‹‹በትግራይ ጠቅላይ ግዛት ስለሚገኙ በውቅር የታሠሩ አብያተ ክርስቲያናት›› በሚል ርእስ ጥናት ከነ ልዩ ልዩ ማስረጃዎች ጋር ያቀረቡት ዶ/ር አባ ተወልደመድኅን ዮሴፍ (1908-1959) በተለያዩ የትግራይ አውራጃዎች 120 የውቅር ሕንፃዎች እንደሚገኙ ገልጸው ነበር፡፡
በጽሑፎቻቸውም እንደሚታየው በትግራይ የሚገኙትን ኢትዮጵያን የሚያኮሯትን የታሪክ የጥበብና የሃይማኖትም ቅርሶች በመግለጻቸው ቀድሞ አስደናቂዎች በሆኑ በላሊበላ ሕንፃዎች የበለጸገውን የአገሪቱን የሥነ ጥበብና የሃይማኖት ታሪክ በበለጠ እንደሚበለጽግ አድርገዋል፡፡
ከእነዚህ 120 ውቅር ሕንፃዎች መካከል አንዷ የሆነችው ማርያም ውቅሮ ቤተ ክርስቲያን ከ50 ዓመት በፊት እንደምትታወቀውና በዶ/ር አባ ተወልደ መድኅን እንደተመዘገበው፣ በዓድዋ አውራጃ በእምባሰነይቲ ወረዳ፣ በአሁኑ አከላለል በማዕከላዊ ዞን በወርዒለኸ ወረዳ በእምባሰነይቲ ንኡስ ወረዳ የምትገኘው እንዳማርያም ውቕሮ ቤተ ክርስቲያን በአራተኛው ምታመት (357 ዓ.ም.) በወንድማማቾቹ ነገሥታት አብርሃ ወአድብሃ መመሥረቷ ይነገራል፡፡
የማርያም ውቕሮ ሕንፃ ሲገለጽ
ከማዕከላዊ ዞን መቀመጫ ከአክሱም ከተማ 112 ኪሎ ሜትር፣ ከሐውዜን 34 ኪሎ ሜትር፣ ከመቐለ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ማርያም ውቕሮ ቤተ ክርስቲያን ከውቅሩ ሕንፃ ጀርባ ለጥ ያለ ሜዳ በመሆኑ በዚያው መስመር የሚመጣ መንገደኛ ወደ ገደል እንዳይወድቅ ከመሥጋት ባለፈ፣ ቤተ ክርስቲያን መኖሩን የሚያሳይ ነገር የለም፡፡ ከሰባት ኪሎ ሜትር ርቀት ከነበለት በሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ በፊት ለፊት የሚመጣም አሻግሮ ቢያይም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑን እንዳይመለከት በዙሪያው ያሉ ኮረብታዎች ይሸፍኑታል፡፡ ከገደላማው ኮረብታ ቀረብ የሚል ተጓዥ ከጠባቦቹ የመግቢያ በሮች ይልቅ ጎልተው የሚታዩት በውቅሩ ከፍታ መስኮት መስሎቹ ሽንቁሮች በውስጡ ቤተ ክርስቲያን እንዳለ ያመለክቱታሉ፡፡
የውቅር ሕንፃው ጠቅላላ ስፋት 20.6 ሜትር በ10.3 ሜትር ሆኖ ከፍታው (ቁመቱ) 6.9 ሜትር ነው፡፡
እንደ አስረጂው መልአከ ሰላም ዓምደብርሃን ገብረፃድቅ አገላለጽ፣ የቤተ ክርስቲያኑ አሠራር ካንድ ቋጥኝ ኮረብታ (ተራራ አከል) ተፈልፍሎ አንድ ወጥ በሆነ ውቅር ድንጋይ የታነፀ፣ ‹‹ዓመደ ጭዳ›› የሚሉት ባለአርባ አራት ምሰሶ ሆኖ በየምሰሶው ማዕዘን ጫፍንና ጠርዝ በተለያየ መልክ የተቀረፁ ሐረጎች፣ የመስቀል የማኅተምና በብዙ ኅብረ ጥበብ የተዋቡ ቅርፆች አሉበት፡፡ በየሕንፃው ግድግዳም የሥነ ሕንፃ ጌጣጌጥና ቅርፃ ቅርፅ ያሉበት ዕፁብ ድንቅ ሕንፃ ነው፡፡ በነባር ስሙ መቅደስ፣ ቅድስትና ቅኔ ማሕሌት ያለው ሲሆን በቅኔ ማሕሌቱ ከራሱ በተያያዘ ከሕንፃው በቅርፅ ተፈልፍሎ የወጣ በአንድ አካል ልክ የተቀረጸ ልዩ መልክና ውበት ያለው ቅርፅ ይታያል፡፡ የደብሩ አለቃ ወይም የአስተዳዳሪ መቆሚያም ማረፊያም ነው፡፡
ከቅኔ ማሕሌት በስተሰሜን በኩል ‹‹ምቅዋም ንግሥት ማርያም›› የሚሉት ሕንፃ አለ፤ የሴቶች መቆሚያና መፀለያ ነው፡፡ በዚያውም ወደ ቅድስት መግቢያ በር አለው፤ መንበረ ታቦቱ ሦስት ሆኖ የቅድስት ማርያም የቅዱስ ሚካኤልና የቅዱስ ገብርኤል ሲሆን ሁሉም በቅርፅ ተፈልፍለው የወጡ ናቸው፡፡
የቅድስት ማርያም መንበር ከላይ ከመንበሩ መጠን ቀስተ ደመና የሚመስል ቅርፅ አለው፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ መግቢያዎች ሦስት በውስጥ ሦስት በውጭ ስድስት ሲሆኑ ባለሁለት ደረጃዎች ናቸው፡፡ የእነዚህ መዝጊያዎች አበው እንደሚናገሩት ከእምባጮ ዕፅ የተሠሩና እስካሁን ድረስ በአገልግሎታቸው ጉድለት የሌለባቸው ጥንካሬያቸው እንደተጠበቀ ይታያል፡፡ መወርመሪያውና መሸጎጫውም አብሮ ካንድ እንጨት የተሠራ ነው፡፡
ከቅኔ ማሕሌቱ በላይ እንደፎቅ ሆኖ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተመቅደስ (ቤተ ጊዮርጊስ) ይገኛል፡፡ በትግራይ ከሚገኙት ውቕር አብያተ ክርስቲያናት አንዱ የሚለየው ባለፎቅነቱ ነው፡፡ ወደፎቁ ለመውጣት አዳጋች በመሆኑ ‹‹ነፍስህን ለፈጣሪ ሰጥተህ ነው በመሰላል የምትወጣው›› ይላሉ፡፡ ከቅድስቱ ውስጥ በስተሰሜን የመድኃኔዓለም ቤተ መቅደስ የሚሉት የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ የንዋየ ቅዱሳቱ ማከማቻ ቤተ መዛግብት አድርገውት ይታያል፡፡ ቤተልሔሙም እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ውቅር ሕንፃ ነው፡፡
ሌላው አስደናቂ ምስጢርና ሁልጊዜም እንደተአምር እየተቆጠረ የሚነገርለት በቅድስቱ ሕንፃ ወለል በግራ በኩል ባለመዝጊያ የሆነ ረዥም የጉድጓድ ዋሻ አለ፡፡ በውስጡ የሚገኝ የምንጭ ውኃ ጥልቅ በመሆኑ በረዥም ገመድ ወይም መጫኛ አድርገው እየቀዱ ለቅዳሴና ለጠበል ይጠቀሙበታል፡፡ ዋሻው ሰፊ ሆኖ በምንጩ ውኃ ዳር የእግር መንገድ አለው ይባላል፡፡ የዕድሜ ባለጸጎች የሆኑት የደብሩ ካህናት የባትሪ ወይም የፓውዛ መብራት ተይዞ በዋሻው ብዙ መንገድ የሚያስኬድ ርቀት እንዳለው ይናገራሉ፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ ከሌሎች ውቅር ሕንፃዎች ሁሉ የበለጠችና ልዩ የሚያደርጋት የቤተ ክርስቲያኑ ሕንፃ የታነፀበት መሣሪያ ‹‹እብነ አድማስ›› የሚባል የሰው እጅ በማይደርስበት የቤተ ክርስቲያኑ ሕንፃ ጣሪያ ላይ በብረት ሰንሰለት ተንጠልጥሎ መገኘቱና መታየቱ ነው፡፡ በዚያ ላይም ‹‹በዕብራይስጥ›› ቋንቋ የተጻፈ ጽሑፍ በቅርጹ ላይ ይገኛል፡፡
አለቱን እያቀለጡ ሕንፃውን የገነቡበት እብነ አድማስ ላይ የተጻፈው ጽሑፍ አለመተርጎሙና አለመጠናቱ የደብሩ አገልጋይ ቄስ ዘማርያም ተክለ ሃይማኖት ያወጋሉ፡፡ ከሦስቱ እብነ አድማሶች አንዱ በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ጊዜ መነቀሱም ይወሳል፡፡
ይሁንና ይህን አስደናቂ የሆነውን የእምባሰነይቲ ውቅሮ ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አናጺው ማነው? የሚል ጥያቄ በሚነሳበት ጊዜ በአካባቢው ሲነገር የኖረ የተለያየ አፈ ታሪክ ቢኖርም በጽሑፍ የተደገፈ ታሪክ እንደሚያስረዳው ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ4ኛው ምታመት ነገሥታቱ አብርሃና አጽብሐ እንደአነጿት ያረጋግጣል፡፡ ከአብርሃና አጽብሐ ገድል የተገኘው የተመረጡ ነገሥት አብርሃ ወአጽብሐ ለዚያ ደብር (ተራራ) ሌላ መቅደስ (ቤተ ክርስቲያን) አነጹ፤ ይህችውም ኦር ለተባለው ወንዝ አቅራቢያ ናት›› ሲል ያስረዳል፡፡ ኦር ማለት በአገሬው ሕዝብ ቋንቋ ወርዒ ማለት ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ወርዒ ለኸ እየተባለ የሚጠራው ነው፡፡
ቱሪስቶችን የምትናፈቀው ማርያም ውቕሮ
ከ1600 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረችው የማርየም ውቕሮ ሕንፃ ምዕመናኑ በተጨማሪ ቱሪስቶችን ይናፈቃል፡፡ እንደ አካባቢው ኅብረተሰብም ሆነ ደርሶ ተመላሹ አገላለጽም በአስደናቂ ሕንፃነቱ ለዓለም ቅርስነት ለመመዝገብ አቅም ያለው ቢሆንም በመሠረተ ልማት በተለይም በመንገድ ችግር ምክንያት ለዓለም ሕዝብ ቀርቶ ለአገር ቤትም ብዙ ሳይታወቅ ቆይቷል፡፡
እንደ መልአከ ሰላም ዓምደ ብርሃን ገብረፃድቅ መግለጫ፣ በሁለት አቅጣጫ በሐውዜንና በዓድዋ ዕዳጋ ዓርቢ በኩል እስከ ነበለት ከተማ ድረስ የነበረው የመንገድ ችግር የተቃለለ ቢሆንም፣ ከነበለት ከተማ እስከ ማርያም ውቕሮ ሕንፃ ድረስ ያለው መንገድ ግን በምስማዕ ወንዝ ድልድይ አለመሠራት ምክንያት ችግሩ አሁንም እንዳለ ነው፡፡ በጋ ሲሆን ብቻ አንዳንድ ጠንከር ያሉ ተሽከርካሪዎች በብዙ ጥንቃቄ እስከ ቤተ ክርስቲያኑ ድረስ ይደርሳሉ፡፡
ሰኔ 21 ቀን 2008 ዓ.ም. በተከበረው ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን በዓል የተገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ይኸንኑ የመንገድ ችግር አንስተው በተለይ መንግሥት ትኩረት እንዲሰጥበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
‹‹የዚህ ታሪካዊ ቦታ ሃይማኖታዊ ቅርስን በማስጠበቅ አካባቢውን በማጽዳትና በማልማት የተጀመረው ልማት ቀጥሎ፣ የአካባቢው ተወላጆችና ምዕመናን እንዲሁም የቅርሱ ተቆርቋሪዎች በመተባበር መንገዱንና ድልድዩን አሠርታችሁ ለቱሪስቶች መስሕብነት የተመቻቸ ማድረግ ይጠበቅባችኋል፤›› ብለዋል፡፡
‹‹ፍጡነ ረድኤት››
ከሺሕ ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው ውቅር ሕንፃ በዘመን እርጅና ሳቢያ አካባቢው ምቹነት አጥቶ ለምዕመናኑም ሆነ ለካህናቱ፣ ለአካባቢው ኅብረተሰብ አዳጋች ሆኖ ዘመንን ቆጠረ፡፡ ለመሳለምም ሆነ ለመጎብኘት የሚደርሰውም ቁጥር አነስተኛ ሆነ፡፡ በአጥቢያው የንግሥ በዓል ኅዳር እና ሰኔ በ21ኛው ቀን ከማይለዩ በቀር፡፡
መልአከ ሰላም ዓምደ ብርሃን በድርሳናቸው እንደገለጹት፣ የቤተ ክርስቲያኑ ቅፅረ ግቢ አፈሩ እየተሸረሸረ አልቆ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ለመግባትና ለመውጣት በተለይ ሌሊት በጨለማ ጊዜ እያንሸራተተ እጅግ ያስቸግር ነበር፡፡ ይህንን የተገነዘቡት የአካባቢው ተወላጅና በዲቁና ያገለገሉት በጎ አድራጊው አቶ ብርሃነ ግደይ ከባለቤታቸው ወ/ሮ ዓለም አረጋዊ ጋር በመሆን ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለደብሩ የሚጠቅሙ የልማት ሥራዎችን ሠርተዋል፡፡ ለዕርዳታ ፈጥነው ደርሰዋል፡፡ ፍጡነ ረድኤት ሆነዋል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መዳረሻ የሚወስደውን ወጣ ገባ አስቸጋሪ መንገድ ለማስተካከል ሰፊ ዓውደ ምሕረት እንዲሆን በአራት ዕርከን ደልድለው ምቹ አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ እንዲሁም ለእንግዶች (ጎብኚዎች) ማረፊያና መጠለያ አዳራሽና አምስት የመኝታ ክፍሎችና የንጽሕና ክፍሎች ማሠራታቸው በምረቃው ወቅት ተወስቷል፡፡
የመሠረተ ልማት ሥራዎቹን ቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ የመረቁ ሲሆን በሥነ በዓሉ ላይ እንደተናገሩትም ‹‹የቀደሙት አባቶቻችን እግዚአብሔር በገለጸላቸው ጥበብ ይህን አስደናቂ ሕንፃ ሠርተው ማስተላለፋቸውን ታሪክ ሲያስታውሳቸው እንዲኖር ሁሉ፣ እንደዚሁም በጎ አድራጊው አቶ ብርሃነ ግደይ በዚህ ታሪካዊ የቅርስና የሃይማኖት ቦታ በሠሩት በጎ ሥራ ሁሉ ታሪክ ለዘላለም እንደሚያስታውሳቸው እሙን ነው፡፡››
የ51 ዓመቱ ድምፅ!
በልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም አሳሳቢነት፣ በውቅር ስለተሠሩት የትግራይ አብያተ ክርስቲያናት ሕንፃዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በ1958 ዓ.ም. በይፋ በዓለም አቀፍ ጉባኤ በሰነዶች በታጀበ ማስረጃ ያስተዋወቁት፣ ነፍስ ኄር ዶ/ር አባ ተወልደመድኅን ዮሴፍ ለፈጸሙት አኩሪ ተግባር በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ላንድሮቨርና ዘመናዊ የሥዕል ማንሻ (ካሜራ) ከወርቅ ሜዳሊያ ጋር ሸልመዋቸው ነበር፡፡ ከጉባኤው አንድ ዓመት በፊት ኅዳር 7 ቀን 1957 ዓ.ም. በአዲስ ዘመን ያሰሙት ድምፅ አሁንም ገደል ማሚቶ ሆኖ ያስተጋባል፡፡ እንዲህ ሲሉ ጽሑፋቸውን ጀመሩ፡፡
‹‹አንድ የውጭ አገር ሰው ሊቅ በቅርብ ዓመታት በአማርኛ ታትሞ በወጣ የኢትዮጵያ ታሪክ መጻፉ ውስጥ፤ ስለ ላሊበላ ሕንፃዎች ብቻ ሲናገር እንዲህ ይላል፤›› ሲሉም ቀጠሉ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያን ታሪክ የሚመረምሩ ሁሉ፤ እስካሁን ድረስ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያንናት የተፈለፈሉበትን የጥበብ ምሥጢር አላገኙትም፡፡ እንደዚህም ማለት በዓለም ላይ ብቻውን የሚገኘውን እንደዚህ ልዩ የሆነውን ሥራ በምን ዓይነት መሥራት እንደቻሉ አላወቁትም ማለት ነው››፡፡ አያይዘውም ሠለሱ፡፡ ‹‹በተጠቀሰው የታሪክ ጸሐፊ ሐሳብ ላይ እርሱን በመከተል ይህንንም ማሰብ እንችላለን፤ ማለት ለግብጽ የፒራሚድ ሐውልቶች ትልቅ መታሰቢያና መለዮ እንደሆኑ ለኢትዮጵያም የአክሱም ሐውልቶችና ከመቶ የሚበልጡ የላሊበላና የሰቆጣ፤ የትግራይ ሕንፃ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አስደናቂዎች መታሰቢያዎችና መለዮዎች እንደሆኑ አሳምረን መገንዘብ አለብን፡፡ ስለዚህም ከሁሉም የዓለም አህጉሮች ኢትዮጵያ አገራችን ብቻ ግምት የሌለው ታሪካዊ ሀብት፣ ማለት ከመቶ በላይ የሆኑ በውቅር የታነፁ አስደናቂዎች አብያተ ክርስቲያናት እንደሚገኙባት ማወቅ፤ ለኢትዮጵያን ሁላችን ወሰን የሌለው ደስታ ሊሰማን ይገባል፡፡
‹‹ተራራዎች እየፈለፈለች፤ በትልቅ ጥበብና ትጋት አለቶችን እየወቀረች የማይፈነቀል የክርስትና ትልቅ እምነቷን በጠንካራው አለትና በተራራዎች ሆድ ውስጥ የመሠረተች ታላቋ ኢትዮጵያ አገራችን፣ በሌሎች የዓለም አህጉሮች የማይገኙ፤ በብዛታቸውና በአስተናነጻቸውም የሚያስደንቁ በውቅር የታነፁ አብያተ ክርስቲያኖቿ በእውነቱ ልትኮራባቸውና ልትደሰትባቸውም የሚገባት ናት፡፡ ዳሩ ግን በዚሁ ምክንያት ለእነኚህ ለምትኮራባቸው ሐውልቶችና በውቅር ለተሠሩ አብያተ ክርስቲያኖቿ ባስፈላጊ ዘዴና ጥንቃቄ ልትይዛቸው ከማርጀትና ከመበላሸትም ልትጠብቃቸው ይገባታል፡፡ እንዲሁም ተገቢ በሆነ ዝግጅት በውቅር ስለ ተሠሩ አብያተ ክርስቲያኖቿ የታተሙ ጽሑፎችን እየዘረጋች በሞላው ዓለም እንዲታወቁ ማድረግ፣ የተባሉት ሐውልቶቿና አብያተ ክርስቲያኖቿ በደንብ ተጠብቀው ለመጪዎች ትውልዶች ማስተላለፍ ኢትዮጵያ ከፍ ያለ ኃላፊነትና የተቀደሰ ተግባር እንዳለባት ልትዘነጋው አይገባትም፡፡››

ማርያም ውቕሮ - ከዓለም የተደበቀው የ1600 ዓመቱ ቅርስ

 የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምና የአርባ ሓራ መድኃኒዓለም ተዐምር


Thursday, July 14, 2016

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያደረጉት ተአምር

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም አሜን
ዛሬ በዓመታዊ የዕረፍታቸው በዓል ታስበው የሚውሉት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡- አምሃራ ሳይንት ቦረና ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም የ5 ሰዓት የእግር መንገድ ከተሄደ በኋላ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ይገኛል፡፡ ይኽ የአቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ጋር የሚያገናኘው ‹‹የእግዜር ድልድይ›› የተባለ አስገራሚ ታሪክ ያለው ድልድይ አለው፡፡ ሁለቱ ቅዱሳን በመንፈስ ተጠራርተው ለመገናኘት ቢያስቡም ታላቁ የወለቃ ወንዝ ሞልቶ በአካል ሳይገናኙ ቀሩ፡፡ በዚህም ሁለቱ ቅዱሳን አዝነው ከወንዙ ወዲያና ወዲህ ሆነው አፈር ተራጭተው ቢመለሱ ያ የተራጩት አፈር በተአምር ድልድይ ሆነ፡፡ ድልድዩን ሁለቱም በበዓታቸው ሆነው በመንፈስ አዩት፡፡ ጠላት ሰይጣንም ይህንን ሲያይ ድልድዩን በትልቅ ሹል ድንጋይ በስቶ ሊያፈርሰው ሲል አባ ጊዮርጊስ በመንፈስ አዩትና ከጋስጫ ተነሥተው በደመና ተጭነው በመሄድ ሰይጣኑን በግዘፈ ሥጋ ገዝተው ያንን አፈርስበታለሁ ያለውን ትልቅ ድንጋይ አሸክመውት ደብራቸው ጋስጫ ድረስ ወስደውታል፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬ በገዳሙ ደወል ሆኖ እያገለግለ ይገኛል፡፡ ድልድዩም እስካሁን ድረስ ለአካባቢው ሙስሊም ማኅበረሰብ ብቸኛው የወለቃ ወንዝ መሻገሪያቸው ሆኖ እያገለገላቸው ይገኛል፡፡

በተአምራት የተሠራው የእግዜር ድልድይ

አባ ጊዮርጊስ የፈለፈሉት ድንቅ ቤተ መቅደስ
 


ሰይጣን ድልድዩን ሊያፈርስበት የነበረው ትልቁ ሹል ድንጋይ አሁን በጋስጫ ገዳም ለመነካካቱ ደወል ሆኖ ያገለግላል
 

ሌላው በእነዚህ ሁለታ ታላላቅ ገዳማት ያየሁት እጅግ አስገራሚ ነገር ቢኖር ሻሾ የሚባለው ነው፡፡ ይኸውም ታማኙ ውሻ ሻሾ በ2006 ዓ.ም እኔ ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም ወደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ለመድረስ የ5 ሰዓት የእግር መንገድ መሄድ ግዴታ በሆነብኝ ሰዓት አሰልቺውን የበረሃ ጉዞ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ስንጓዝ ሙሉውን የ5 ሰዓቱን መንገድ ይመራን የነበረው ታማኙ ውሻ ሻሾ ነበር፡፡ ደክሞን ስናርፍ አብሮን እያረፈ፣ መሄድ ስንጀምርም አብሮን ከፊት ከፊት እየተራመደና መንገዱን እየመራ እዛው ገዳሙ አደረሰን፡፡ ሻሾ ዛሬ ከሰው ይበልጥ ናፈቀኝ፡፡ የጻድቁን የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን በረከት አንድም ታማኙን ሻሾን ለማግኘት መስከረም ላይ ከግሸን መልስ ለመሄድ አስቤያለሁና አምላከ ቅዱሳን ይፍቀድልኝ፡፡

ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም እስከ አባ ጊዮርጊስ ገዳም ድረስ ያለውን የ5 ሰዓት የእግር መንገድ ከፊት ከፊት እየመራ በረሃውን አቋርጦ የወሰደኝ የገዳሙ ታማኝ ውሻ ሻሾ- ከገዳሙ በቅርብ ርቀት ላይ ከደረሰ በኃላ ሲያሳርፈን፡፡


የግሸን ተጓዞች ይኽን አጋጣሚ ብትጠቀሙ በረከቱ ዕጥፍ ድርብ ይሆንላችኃል፡፡ ከደሴ በግማሽ ቀን ወግዲ የምትባል ከተማ በማደር በቀጣዩ ቀን በአሕዛብ የተከበቡትንና እጅግ አስገራሚ የሆኑትን የአባ ጽጌ ድንግል ገዳምንና የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳምን መሳለም ይቻላል፡፡ እዛው አካባቢ ደግሞ ጸበላቸው ውስጥ እንጨት ሲነከርበት መቁጠሪያ አድርጎ የሚሰጠውን የአቡነ ገብረ እንድርያስን ገዳም መሳለም ይቻላል፡፡

Wednesday, July 13, 2016

ከሰማይ መና የሚወርድበት ሰረድኩላ ሚካኤል

ከሰማይ መና የሚወርድበት ሰረድኩላ ሚካኤል አስተዋሽ ያጣ ሊታወቅ የሚገባ ብዙ ታሪክ ያለው ቤተክርስቲያኑ ፈርሶ የሚሰራው የሚረዳው የሚያስታዉሰው ያጣ ተምረኝዉ የቅዱስ ሚካኤል ገዳም ::

 
መንዝ እመጋ ቆላ አካባቢ ሰረድኩላ ቅድስ ሚካኤል :-
ይህን ገዳም እስራኤላዎቹ በደመና መጥተዉ ና ክንፍ ያላቸው ከመሰረቱት ከ፬4ቱ ቅዱሳን አንዱ /ናአድ/ የመሰረቱት ገዳም ነው፡፡
ይህ ገዳም ትልቅ ዋሻ በቤተክርስቲያኑ አካባቢ ይገኝል፡፡

ዋሻው ውስጥ ሲገቡ ያልፈረሱ ብዛትያላቸው ክንፍ ያላቸውና ክንፍ የሌላቸዉ አፅመ ቅዱሳን/ይታያሉ፡፡በዚህ ዋሻ ውስጥ ማንም ሰው ሂዶ ሊያየው የሚችል /መና/ ከሰማይ ይወርዳል፡፡በዚያ አካባቢ ታይቶ የማይታወቅ አህል ነገሮችአና መና በዋሻው ውስጥ በብዛት ተንጠልጥለው እና ዙሪያው ሁሉ፡ ሽንብራ;አተር;ባቂላ ና የተለያዩ የማይታወቁ ጥራጥሪዎች ና /የኮክ ፍሬ/ ይታያሉ፡፡ 


የሚገርመው እዚያ አካባቢ ኮክ አያቁም አይበቅልም፡፡አይተውትም አያቁም፡ዋሻው ውስጥ ሲገብ በብዛት የኮክ ፍሬ ይታያል፡፡የተለያዩ ቅርሶች በዋሻው ውስጥ ይታያሉ፡፡ ይህን ቦታ ቤተክርስቲያናችን አለማሳወቋ በጣም ያሳዝናል እግዚአብሔር ግዜ አለው ለዚህ ቦታ ወገኖቺ በቅዱስ ሚካኤል ስም ይህን ቦታ አሳውቁ የማይታወቁ ቅርሶች ያለበት ቦታ ነው፡፡እንጠብቀው፡እንከልለዉ፡እንከባከበው አደራ እላለሁ ፡፡ ቤተክርስቲያኑ አርጅቶ በራሱ ግዜ ፈርሶ አስተዋሽ አጥቶ ፡፡በአዲስ መልክ ለመስራት የአገሩ ሰወች ኮሚቴ አቋቁመው በመለመን ላይ ናቸው፡፡

የሚካኤል ወዳጆች ሚካኤልን የምትወዱ:የምትዘክሩ በቅዱስ ሚካኤል ስም እርዱት እናሰራው በጣም ታዕምር ያየሁበት እና የቅዱሳን ቦታ ነው፡፡/የሰረድኩላ ቅዱስ ሚካኤል በቤታችን ይግባ;ሀሳባችን ያሳካልን፡፡አሜን!!!
ቦታዉ፡-ከአ/አ ሰሜን ሸዋ መንዝ ሞላሌ በእመጋ ኡራኤል ኢየሱስ ገዳም አካባቢ፡መንዝ ከሞላሌ ከተማ የ፭5ሰዓት የእግር መንገድ ሰረድኩላ ሚካኤል ይባላል፡፡

ጩጊ ማርያም- ከጸበሉ ጠጥተው ስጋቸው ያልፈረሰ ፍየሎች

Friday, July 8, 2016

የሸንኮራው ዮሐንስ ተነግሮ የማያልቀው ተአምር!!!!!!!!!



ሰውነቴ በለምጽ የተመታው ነፍስ ሳላውቅ በህጻንነቴ ነው የምትለዋ የጎንደርዋ አጸደ ማርያም ነፍስ ሳውቅ ማፈር ጀመርኩኝ ትምህርቴንም አቁዋርጩ ወደ መሐል ሐገር መጣው ሰው ቤት ለመግባት ማን ይቅጠረኝ ፊቴን ሲያዮ ይደነግጣሉ ከሰው ተጠግቼ በቆሎ መሸጥ ጀመርኩኝ የዛሬ አመት ክረምቱ ሲገባ አንዲት ሴት ልትገዛኝ መጥታ ስለ ሸንኮራ ነገረችኝ አቅም የለኝም ለመሄድ ስላት ጸበልና እምነቱን ሰጠችኝ ማታ ሰውነቴን ተቀብቼው አደርኩኝ አታምኑኝም ለድህነቴ ምክንያት ሁለቱም እጆቼ ጠዋት ስነሳ ሌላ መልክ አምጥተዋል ደነገጥኩኝ ሰው ሲያየኝ ደነገጠ ምን መድሐኒት ነው አሉኝ ጨርቄን ማቄን ሳልል ሸንኮራ መጣው መጥምቁ ምን ተስኖት ሰውነቴ በሙሉ ዳነ ከሰው እኩል አቆመኝ አዲስ አበባ ስመጣ የሚያውቁኝ ጠፋውባቸው መላ አካሌ በለምጽ ተመቶ ነበርና ስድን አዲስ ሌላ ከለር ሌላ ሰው ሆንኩኝ መጥምቅዬ ከጌታው አማልዶ ምንም የማላወቀውን በሸንኮራው የሰርክ ጉባኤ ትምህርት ለንስሐ ለስጋ ወደሙ በቃው እደጁ ያወቁኝ እናት በግል ሆቴላቸው ቀጥረውኝ ጥሩ ደሞዝ አገኛለው ከዝናብና ብርድ ዳንኩኝ ትላንት በበዓሉ ግቢው በእልልታ ስታቀልጥ ነበህ እህታችን እኔን የዳበሰ የዮሐንስ አምላክ ሁላችሁን ይዳብሳችሁ ትላለች አሜን

ተአምር በ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ከርስቲያን /ሽሬ/


Wednesday, July 6, 2016

መጥምቁ ዮሐንስ ከዘመኑ እሳት አወጣኝ


አጸደ ማርያም እህታችን በአዲስ አበባ አንድ ጭፈራ ቤት ውስጥ በዘፋኝነት ትሰራ ነበር የስራ ባልደረባዋ በኤችአይቪ በሽታ ተይዛ
ወደ ሸንኮራ ጸበል ትሄዳለች አጸደ ማርያም እህትዋን ለመጠየቅ ሸንኮራ ወርዳ ሳለ የዮሐንስን ታሪክ አንገቱም በዘፈን ምክንያት እንደተቆረጠ ትሰማለች ይልቁንም ጉዋደኛዋ ያቀረበችላት የተመርመሪ ጥያቄ ያስጨንቃታል አዲስ አበባ መጥታ ስትመረመር የHiv ቫይረስ በደምዋ ይገኛል ደጋግማ ከ3ወራት ቆይታ በሁላ ስትመረመር ለውጥ የለም በመጨረሻ ወደ ሸንኮራ ዮሐንስ ጸበል በመምጣት ንስሐ ገብታ ጸበልዋን ለ1 አመት ስትከታተል ቆይታ ድጋሚ ለምርመራ ስትመጣ ደምዋ ንጹህ እንደሆነ ይነገራታል በስእለትዋ መሰረት ስጋ ወደሙ ተቀብላ ከቀደመው ህይወትዋ እራስዋን አግላለች መጥምቁ የፈወሳት በሽታዋ ብዙ ነው ከዘፋኝነት 13 አመት ሲጋራና ጫት ስትወስድም ነበር ከዝሙት መንፈስ ከጥንቁልና አምልኮ ተላቃለች ያቁዋረጠችውን ትምህርት ቀጥላ ሸንኮራ ባወቀቻት እህት እርዳታ ድግሪዋን ይዛ ትዳር መስርታ ልጅም ወልዳ አዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ ትኖራለች ያችም ቀድማ የታመመች እህታችን በሽታዋ ድና ሰሜን ወሎ አንድ ገዳም ውስጥ በምናኔ ትኖራለች ክብር ለዮሐንስ


ለክርስትና ስጦታ መተት በአሻንጉሊት ተቀብሮ የተሰጣት እናት - ድንቅ ተዓምር